Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዓለም ምርጥ አትሌት ሽልማትን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ከስቴዲየም ውጭ ባሉ ውድድሮች ባሳየችው ድንቅ የሆነ ብቃት የዓመቱ ምርጥ አትሌት መባሏን የዓለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል። አትሌት ትዕግስት በሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት እንደሆነች ይታወቃል። ከቀናት በፊት ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በስፖርታዊ ጨዋነት ማሸነፏ የሚታወስ ነው።
Read More...

ማህበሩ የ7ኛ ሣምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር በ7ኛ ሣምንት ጨዋታዎች የተላለፉ የዲስፕሊን ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ በሣምንቱ መርሐ ግብር በተደረጉ ሠባት ጨዋታዎች ስድስቱ በመሸናነፍ እንዲሁም አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 16 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ተቆጥሯል። በተጨማሪም 28 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ…

ዝላታን ኢብራሂሞቪች የኤሲ ሚላን የቦርድ አባል ለመሆን መስማማቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድናዊው አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች የጣሊያኑን ኤሲ ሚላን በቦርድ አባልነት ለመቀላቀል መስማማቱ ተገልጿል፡፡ እስከ 41 ዓመቱ ድረስ በኢንተርናሽናል እግር ኳስ የዘለቀው ግዙፉ አጥቂ ባለፈው ክረምት ራሱን ከእግር ኳስ ዓለም ማግለሉ የሚታወስ ነው፡፡ ከእግር ኳሱ ከተገለለ በኋላ ከክለቡ ጋር ግንኙነቱን ያላቋረጠው…

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ወደ አሸናፊነት ሲመለስ ዌስትሃም በሰፊ የጎል ልዩነት ተሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል። 11 ሰአት ላይ በተደረጉት ጨዋታዎች ኤቨርተን ከቼልሲ፣ ፉልሃም ከዌስትሃም ዩናይትድ እንዲሁም ሉተን ታዎን ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ተገናኝተዋል። ከፋይናንስ ህግ ጥሰቶች ጋር በተያያዘ 10 ነጥቦች የተቀነሱበት የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል፡፡ ዛሬ 9፡00 ሰአት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የድል ጎሎች ባሲሩ ኡመር እና ሲሞን…

ከጥር ወር ጀምሮ የአበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ይደረጋል- ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶች ከጥር ወር 2016 ጀምሮ የአበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን አስታወቀ። ለፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶችም ከወዲሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነው የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬከተር መኮንን ይደርሳል…

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቡዳፔስት ላይ በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊት የሆነችው እና በአሁኑ ጊዜ ለሆላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሐሰን በሩጫ ወቅት መውደቋ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም…