Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በሞሮኮና ሊቢያ በአደጋ ህይወታቸው ያለፉትን ለመዘከር ተጫዋቾች ጥቁር ባጅ ያደርጋሉ – ፕሪሚየር ሊጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሮኮ የመሬት መንቀጥቀጥና በሊቢያ የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ያጡትን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለመዘከር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁሉም ተጨዋቾች ጥቁር ባጅ በክንዳቸው ላይ እንዲያደርጉ መወሰኑን ሊጉ አስታውቋል፡፡ የእንግሊዝ ፕረሚየር ሊግ በማህበራዊ ትስስር ገፁ÷ በቅርቡ በሞሮኮ እና በሊቢያ በተከሰቱት  አሳዛኝ  የተፈጥሮ አደጋዎች ፕሪሚየር ሊጉ በእጅጉ አዝኗል ብሏል፡፡ ከጨዋታው በፊት አሳዛኙ ክስተት ይታወሳል ያለው ፕሪሚየርሊጉ÷ ከጥቁር ባጁ በተጨማሪ ክለቦች እና ተጋጣሚዎቻቸው በሞሮኮ…
Read More...

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የፊታችን ጥቅምት 17 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የፊታችን ጥቅምት 17 ቀን እንደሚጀመር ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ፌደሬሽኑ የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚጀምርበትን ቀን እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ለተሳታፊ ክለቦች ማሳወቁ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ መሰረትም የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብሩ…

ፍቅረማሪያም ያደሳ በአፍሪካ ዞን የቦክስ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ በፍጻሜ ይጫወታል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ቦክሰኛ ፍቅረማሪያም ያደሳ (ጊችሮ ነብሮ) በአፍሪካ ዞን የኦሊምፒክ ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ ዛሬ በፍጻሜ ይጫወታል። ፍቅረማሪያም በዛሬው እለት በ57 ኪሎ ግራም ከናይጀሪያዊው ቦክሰኛ ጋር የፍጻሜ ጨዋታውን ያደርጋል። በፍጻሜ ጨዋታው አሸናፊ መሆን ከቻለም ኢትዮጵያን በፓሪሱ ኦሊምፒክ ይወክላል። በሴኔጋል…

አርቢትር ባምላክ ተሰማ የ2024 አፍሪካ ዋንጫን ከሚመሩ ዋና ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 3 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የኮትዲቯሩን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞችን ዝርዝር ይፋ አድርግል። በዝርዝሩ የመሀል፣ ረዳት፣ የቪዲዮ ረዳት ዳኞች፣ ቴከኒካል ኢንስትራክተሮች፣ የVAR ቴክኒሻኖች እና የአይቲ ባለሙያዎች ተካተዋል። 85 ባለሙያዎች ይፋ በሆኑበት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊው…

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሆቴሉን በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ማረፊያ እንዲሆን ፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሞሮኮ የሚገኘው የግል ሆቴሉ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ማረፊያ እንዲሆን ፈቅዷል፡፡ ቶክ ስፖርት እንዳስነበበው÷ በሞሮኮ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ከተሰማ በኋላ ፖርቹጋላዊው የእግርኳስ ኮከብ በማራካሽ የሚገኘው ሆቴሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ክፍት ማድረጉን አስታውቋል፡፡ “ፔስታና ሲ አር…

ሽመልስ በቀለ መቻልን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ጷጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገር ውጭ በተለያዩ ሀገራት ክለቦቸ ለ10 ዓመታት ሲጫወት የቆየው ሽመልስ በቀለ ለመቻል ፈርሟል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ወደ ግብፅ ያመራ ሲሆን÷ በግብፅ ለሚገኙ ሶስት የተለያዩ ክለቦች መጫዎች ችሏል፡፡ በፔትሮጀት ስድስት ዓመታትን፣በምስሪ ላል መቃሳ ሁለት ዓመታትን በኤል ጎውና ለአንድ…

በኒውካስል ግማሽ ማራቶን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ኒውካስል በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ አሸንፏል፡፡ አትሌት ታምራት ቶላ ርቀቱን 59 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሙክታር እድሪስ ደግሞ ርቀቱን 1 ሰዓት 01 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን…