ስፓርት
ሞሮኮ ታንዛኒያን 3 ለ 0 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በምድብ ስድስት የሚገኙት ሞሮኮ እና ታንዛኒያ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
ሮማን ሳዩስ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ለእረፍት የወጣችው ሞሮኮ÷ በሁለተኛው አጋማሽ ኡናሂ እና የሱፍ ኤል ነስሪ ባስቆጠሯቸው ተጨማሪ ጎሎች ጨዋታውን 3 ለ 0 ረትታለች፡፡
በ70ኛው ደቂቃ ኖቫቲስ ሚሮሺን በቀይ ካርድ ያጣችው ታንዛኒያ ቀሪዎቹን ደቂቃዎች በ10 ተጫዋቾች ለመጨረስ ተገዳለች።
ሞሮኮ ኳታር ባስተናገደችው 2022 የዓለም ዋንጫ እስከ ግማሽ ፍጻሜ በመድረስ ብርቱ ፉክክር ማድረጓ…
Read More...
መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
9፡00 ሠዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማን የገጠመው መቻል ከንዓን ማርክነህ እና በኃይሉ ግርማ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
እንዲሁም 12፡00 ሠዓት ላይ ኢትዮጵያ መድንን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመመራት…
ናሚቢያ ቱኒዚያን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 5 ጨዋታ ናሚቢያ ቱኒዚያን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈች፡፡
ናሚቢያን አሸናፊ ያደረገችውን ግብ ሆቶ በ88ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
በዚሁ ምድብ የሚገኙት ማሊና ደቡብ አፍሪካ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
ቀደም ብሎ በተደረገ የምድብ 4 ጨዋታ ቡርኪናፋሶ…
ቡርኪናፋሶ በተጨማሪ ሰዓት ባስቆጠረችው ግብ ሞሪታኒያን አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ 4 የማጣሪያ ጨዋታ ቡርኪናፋሶ በተጨማሪ ሰዓት ባስቆጠረችው ግብ ሞሪታኒያን 1 ለ 0 አሸነፈች።
ለቡርኪናፋሶ የማሸነፊያ ግብን በርትራንድ ትራኦሬ በ96ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል፡፡
በአፍሪካ ዋንጫ በምድብ 5 ጨዋታዎች ምሽት 2 ሰዓት ላይ ቱኒዝያ ከናሚቢያ እንዲሁም ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ…
ጆዜ ሞሪንሆ ከሮማ አሰልጣኝነታቸው ተባረሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጆዜ ሞሪንሆ ከሮማ አሰልጣኝነታቸው መባረራቸው ተሰምቷል፡፡
ለስንብታቸው የቡድኑ ውጤት ማጣት እና ከዳኞች ጋር የሚፈጥሩት አለመግባባት ምክንያት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ሮማ በሴሪአው ካደረጋቸው የመጨረሻዎቹ ስድስት ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በኮፓ ኢታሊያም በላዚዮ መሸነፉ…
በአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን እና ጊኒ በአቻ ውጤት ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን እና ጊኒ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
የካሜሮንን ብቸኛ ግብ ማሪ ማግሪን ሲያስቆጥር ÷ የጊኒን ደግሞ ሞሃመድ ባዮ አስቀጥሯል፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ መርሐ- ግብር ሲቀጥል ምሽት 5 ሰዓት አልጀሪያ ከአንጎላ ይጫወታሉ፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ባሕር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ባሕር ዳር ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡
ቀን 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን ግቦች ጊት ጋትኩት እና ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው የባሕርዳር ከተማው ተከላካይ ያሬድ ባዬ በፈጸመው ጥፋት በቀይ…