Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በለንደን ዳይመንድ ሊጉ ጉዳፍ ፀጋየ  አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን ዳይምንድ ሊጉ የ5 ሺህ ሜትር ወድድር  አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ ድል ቀንቷታል፡፡ ጉዳፍ  ርቀቱን ለመጨረስ 14 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ የፈጀባት ሲሆን ተቀናቃኞቿን ሲፈን ሀሰን እና ብያትሪስ ቺቤትን በመቅድም ነው የ5 ሺህ ሜትር እርቀቱን በበላይነት ያጠናቀቀችው፡፡ በርቀቱ ኬንያዊቷ ብያትሪስ ቺቤት 2ተኛ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ  እና ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው አትሌት ሲፈን ሀሰን 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡ የኦሪገኑን ድርብ ድል በቡዳፔስት ለመድገም እየተዘጋጀች  የምትገኘው…
Read More...

በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት አሸነፈ። በውድድሩ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። ውድድሩን አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት በ12 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ከ18 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት…

አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ጫማ ሰቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክለቦች እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለበርካታ አመታት አገልግሎት የሰጠው ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቅሏል፡፡ ሳላዲን ሰይድ ለ15 ዓመታት በብሔራዊ ቡድን እና እና በተለያዩ ክለቦች መጫዎት የቻለ ሲሆን በ37 ዓመቱ ጫማ መስቀሉን ለሶከር ኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡ አጥቂው በ2014/15 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ…

በዓለም የውሀ ስፖርቶች ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽኝት ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛው የዓለም ውሀ ስፖርቶች ሻምፒዮና ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ሽኝት ተደረገለት። በጃፓን ፎካካ በሚካሄደው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአንድ ወንድና ሴት አትሌቶች በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ እና ቢራቢሮ ትካፈላለች። የዓለም ውሃ ሻምፒዮና ተወዳዳሪዎች ከሁሉም ክልሎች የመጡ እና የማጣሪያ ውድድር…

ቤንጃሚን ሜንዲ ዳግም ወደ እግር ኳስ ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የማንቼስተር ሲቲ ተካላካይ ቤንጃሚን ሜንዲ ከፍርድቤት እንግልት በኋላ ዳግም ወደ እግር ኳስ ተመልሷል፡፡ በዚህ ክረምት ወር ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት የተጠናቀቀው ሜንዲ ከቀናት በፊት በፈረንሳይ ሊግ ዋን ለሚገኘው ሎሬንት ክለብ መፈረሙ ተሰምቷል፡፡ የ29 ዓመቱ የግራ ተከላካይ ቤንጃሚን ሜንዲ…

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ኢንተር ሚላን በኦናና ዝውውር ሥምምነት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ ካሜሩናዊውን ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ለማስፈረም ሥምምነት ላይ መድረሱ ተሰማ። ክለቡ ለግብ ጠባቂው 47 ነጥብ 2 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ገንዘብ ለመክፈል ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር ሥምምነት ላይ ደርሷል ነው የተባለው። በቅድሚያ 43 ነጥብ 8 ሚሊየን ፓውንድ…

በፖላንድ የዳይመንድ ሊግ አትሌት ሂሩት መሸሻ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳይመንድ ሊግ 8ኛ ከተማ በሆነችው የፖላንዷ ሲሌሲያ ከተማ በተደረገ ውድድር አትሌት ሂሩት መሸሻ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በ1 ሺህ 500 ሜትር በተደረገ ውድድር በሴቶች ሂሩት መሸሻ 3 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት ስታሸንፍ በርቀቱ የግሏን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ብርቄ…