ስፓርት
በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ጋምቢያን 3 ለ 0 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሴኔጋል ጋምቢያን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
የሴኔጋልን የማሸነፊያ ግቦች ፔፔ ጉዮ እና ላሚን ካማራ አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው የጋምቢያው ተከላካይ ኢብራሂማ አዳምስ በፈፀመው ያልተገባ ባህሪ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ መርሐ ግብር ምሽት መካሄዱን ሲቀጥል ምሽት 2 ሰዓት ካሜሩን ከጊኒ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት አልጀሪያ ከአንጎላ ይጫወታሉ፡፡
Read More...
በአፍሪካ ዋንጫ ኬፕ ቨርዴ ጋናን 2 ለ1 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኬፕ ቨርዴ ጋናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈች።
የኬፕ ቨርዴን የማሸነፊያ ግቦች ሞንቴሮ እና ሮድሪጌዝ ሲያስቆጥሩ፥የጋናን ብቸኛ ግብ ደግሞ ጂኩ አስቆጥሯል።
በተመሳሳይ በምሽት 2 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ግብፅ እና ሞዛምቢክ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ምሽት 2 ሰዓት ላይ…
በአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የሁለተኛ ቀን ውሎ የተገናኙት ናይጄሪያ እና ኢኳሪያል ጊኒ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ቪክቶር ኦሲሜን ለናይጄሪያ እንዲሁም ጆሴፍ ማሽን ለኢኳሪያል ጊኒ ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ መርሐ- ግብሮች ምሽት መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ 2፡00 ሰዓት ላይ ግብጽ ከሞዛምቢክ ይገናኛሉ፡፡
በተመሳሳይ…
የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር መጠናቀቁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
በ6 ኪሎ ሜትር የወጣት ሴቶች ሩጫ አትሌት የኔዋ ንብረት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስታሸንፍ አሳየች አድነው በተመሳሳይ ከንግድ ባንክ 2ኛ እንዲሁም ሽቶ ጉሚ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡…
በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ አስተናጋጇ ኮትዲቯር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ አስተናጋጇ ኮትዲቯር ጊኒ ቢሳውን 2 ለ 0 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ አግኝታለች።
ለኮትዲቯር የማሸነፊያ ግቦቹን ገና ጨዋታው በተጀመረ አራተኛ ደቂቃ ላይ ፎፋና ሲያስቆጥር፥ ሁለተኛዋን ግብ ደግሞ ክራሶ ከእረፍት በኋላ 58ኛ ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ድል ቀናው
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት ጨዋታውን በሜዳው ያደረገው ቼልሲ ድል ቀናው።
ፉልሃምን ያስተናገደው ቼልሲ ከእረፍት በፊት ፓልመር በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠረው ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በዚህም ነጥቡን 31 በማድረስ በፕሪሚየር ሊጉ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሊጉን…
በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚያቸውን ረቱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ወልቂጤ ከተማን እንዲሁም ወላይታ ድቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸንፈዋል፡፡
9፡00 ሠዓት ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ ከመረብ ባገናኛት ብቸኛ ጎል ፋሲል ከነማ ወልቂጤ ከተማን አሸንፏል፡፡
ዐፄዎቹ 1 ለ0 ማሸነፋቸውን ተከትሎም…