ስፓርት
በሪጋ በሚካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውን አትሌቶች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስት ርቀቶች በላቲቪያ ሪጋ ነገ በሚካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ፡፡
5፡50 ላይ በሚካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር የሴቶች ውድድር አትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ሲሳተፉ÷ በዚሁ ርቀት 12፡15 ላይ በሚካሄደው የወንዶች ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ሀጐስ ገ/ሕይወት ይካፈላሉ፡፡
7፡00 ላይ በ1 ማይል ርቀት በሚከናወነው የሴቶች ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ኃይሉ የሚሳተፉ ሲሆን÷ በተመሳሳይ ርቀት 7:10…
Read More...
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጀመራል፡፡
ፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9፡00 ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ ነው የሚጀመረው፡፡
የነገው የጨዋታ መርሐ- ግብር ሲቀጥል 12፡00 ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በበርሊን የሴቶች ማራቶን ክብረወሰን ለሰበረችው አትሌት ትዕግስት አቀባበል ተደረገላት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ49ኛው የበርሊን ሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በማሻሻል ላሸነፈችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላታል።
አትሌቷ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ስትገባ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር…
ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆነ፡፡
የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የአንደኛ ዙር ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከብሩንዲ ጋር አድርጓል፡፡
ሉሲዎቹ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በመለያ ምት 5 ለ…
የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባው ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳሱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አመራሮችና ስራ አስፈፃሚ አባላት ጋር በእግር ኳሱ ዕድገት…
በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ለፍጻሜ ደረሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡
በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የተጫወተው ሃድያ ሆሳዕና በመለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል።
በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና በመለያ ምት 5 ለ…
የሰሜን ለንደን ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐር ያደርጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
ቶተንሃም የጨዋታ ብልጫ በወሰደብት የሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ክርስቲያን ሮሜሮ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢችልም ሰን ሁንግ ሚን ቶተንሃምን አቻ አድርጎ የመጀመሪያውን አጋማሽ አንድ አቻ አጠናቅቀዋል፡፡…