Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት ነው ክብረወሰኑን የሰበረችው። ኬኒያዊቷ አትሌት ብሪግድ ኮስጌይ በፈረንጆቹ 2019 በ2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት ይዛው የነበረውን ሪከርድ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ሰብራለች፡፡ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የበርሊን ማራቶንም 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በመግባት የዓለምን ሦስተኛውን…
Read More...

ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ሲቲ÷ ፊል ፎደን እና ኤርሊንግ ሃላንድ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው ተጋጣሚውን የረታው፡፡ ሮድሪ በ46ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡ በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ክርስታል ፓላስ…

ሉሲዎቹ ከቡሩንዲ አቻቸው ጋር ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታው 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂደዋል ። በዚህም ሉሲዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ በረድኤት አስረሳኸኝ ጎል ተጋጣሚያቸውን 1 ለ 0 መምራት ችለው ነበር፡፡ ሆኖም በሁለተኛው አጋማሽ የብሩንዲ ሴቶች ብሄራዊ…

ጁሌያን ኔግልስማን የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የባየርሙኒክ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በአንድ ዓመት ኮንትራት የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል፡፡ የ36 ዓመቱ አሰልጣኝ በቅርቡ የተሰናበቱትን የቀድሞው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በመተካት ነው ብሄራዊ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት የተረከቡት፡፡ ከስምምነቱ በኋላ ኔግልስማን…

ፊፋ የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊፋ የካፍ ዞን የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚሁ የፊፋ ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በካፍ እውቅና ስር ከሚገኙ 50 ሀገራት 42ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ከዓለም ደግሞ 142ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ሞሮኮ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ፣ሴኔጋል፣ቱኒዝያ፣አልጀሪያ፣እና ግብፅ በቅደም…

ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ቀን 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያካሂዳል ። በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ÷ 26 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን ከጳጉሜን 3 ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲያደርግ ቆይቷል። ከሀገር…

በሪጋ 2023 የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በላቲቪያ ሪጋ በሚካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የማሸነፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በጎዳና ውድድሩ አምስት የዓለም ሪከርድ የሰበሩ አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን÷ የኦሎምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮን አትሌቶችን ጨምሮ 347 አትሌቶች በስድስት ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡ ከመስከረም 20 እስከ 21 ቀን 2016…