ስፓርት
የሜሲ10 ቁጥር መለያ በሌላ ተጫዋች እንደማይለበስ አርጀንቲና አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዮኔል ሜሲ እግር ኳስ ካቆመ በኋላ 10 ቁጥር መለያው በሌላ ተጫዋች ሊለበስ እንደማይችል የአርጅንቲና እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ክላውዲዮ ታፒያ÷የሊዮኔል ሜሲ10 ቁጥር መለያ ለዘላለም ተከብሮለት ይኖራል፤እኛ ለእርሱ የምናደርግለት ትንሹ ነገር ይህ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ከፈረንጆቹ 1986 በኋላ ለ3ኛ ጊዜ ባነሳችው የኳታሩ ዓለም ዋንጫ 7 ግቦችን በማስቆጠር ለቡድኑ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱ ይታወሳል፡፡
ሀገሩ የዓለም ዋንጫን…
Read More...
ኡጋንዳዊው አትሌት በኬንያ መኪና ውስጥ ሕይወቱ አልፎ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡጋንዳዊው አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት በኬንያ መኪና ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተሰምቷል፡፡
በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች በ3 ሺህ መሰናክል ሀገሩን የወከለው አትሌት ኪፕላጋት አንገቱና ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ሕይወቱ ማለፉን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የ34 ዓመቱ ኪፕላጋት ታዋቂ አትሌቶች ልምምድ በሚያደርጉባት…
ፉልሃምና ቶተንሃም ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ጨዋታ በሜዳቸው ያደረጉት ፉልሃምና ቶተንሃም ድል ቀናቸው።
አርሴናልን ያስተናገደው ፉልሃም በ29ኛውና በ59ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ከተመሪነት ተነስቶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የማሸነፊያ ጎሎቹን ሄሜኔዝ እና ዲ ኮርዶቫ-ሬይድ ሲያስቆጥሩ፤ የአርሴናልን ጎል ደግሞ…
2023 ለሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ታሪካዊ ዓመት ነበር ተባለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንጆቹ 2023 ለሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር የተለየ ዓመት እና ታሪካዊ እንደነበረ የዓለም አትሌቲክስ ገለጸ።
በዓመቱ የርቀቱ ክብረ ወሰን ሁለት መሰበሩን ጠቅሷል።
ከዚህ በተጨማሪም የርቀቱ የምንጊዜም 10 ፈጣን ሰዓት መካከል ስድስቱ በዚህ ዓመት የተመዘገበ መሆኑን የዓለም አትሌቲክስ በማህበራዊ ትስስር ገጹ…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ፣ ማንቼስተር ሲቲ እና አስቶንቪላ አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ፣ ማንቼስተር ሲቲ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡
9፡30 ከሜዳው ውጭ ሉተን ታውንን የገጠመው ቼልሲ 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
ኑኖ ማዱዌኬ እና ኮል ፓልመር (ሁለት) የቼልሲን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ኤሊያህ አደባዮ እና ሮዝ ባርክሌይ የሉተንን ሁለት ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡…
በአዲስ አበባ ደርቢ ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥብ አሳክቷል፡፡
9፡00 ላይ በተደረገው ተስተካካይ ጨዋታ የቡናማዎቹን ብቸኛ ጎል ጫላ ተሺታ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ለመጋራት በተደጋጋሚ ያደረገውን ሙከራ ወደ ውጤት መቀየር ሳይችል ቀርቷል፡፡
ውጤቱን…
አንድሬ ኦናና በካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ተካተተ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በኮትዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ በሚሳተፈው የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ዝርዝር ውስጥ ተካትቷል፡፡
ኦናና በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሀገሩ ከአሰልጣኝ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በጊዜያዊነት ከብሔራዊ ቡድኑ ርቆ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ካሜሩን በአጠቃላይ 27 ተጫዋቾችን ይፋ ያደረገች ሲሆን÷…