ስፓርት
በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ ደረሱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ቢንያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ለፍጻሜ አልፈዋል፡፡
የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር 6 ሰዓት ከ10 ላይ ተካሂዷል፡፡
በዚህም አትሌት ሐጎስ በምድብ አንድ 2ኛ እንዲሁም በምድብ ሁለት ቢንያም መሐሪና አዲሱ ይሁኔ በቅደም ተከተል 2ኛ እና 8ኛ ደረጃን በመያዝ ለፍጻሜ አልፈዋል፡፡
በተመሳሳይ አትሌት ብርቄ ኃየሎም በ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ለግማሽ ፍፃሜ አልፋለች፡፡
Read More...
ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡
በዚሁ መሠረት ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በሚካሄደው 3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ ይሳተፋሉ፡፡
እንዲሁም ቀን 6 ሠዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው…
በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በፓሪስ ኦሊምፒክ በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም፡፡
በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ።
ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት ከ5 ላይ በተካሄደው 1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።
በዚህም ጉዳፍ…
ኢትዮጵያ የምትካፈልበት 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ምሽት 4 ሠዓት ከ10 ላይ ትሳተፋለች፡፡
በዚሁ መሠረት በፍጻሜ ውድድሩ አትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ ዓለማየሁ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡
ከትናንት በስቲያ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ሎሚ 9 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ ከ73 ማይክሮ…
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በይፋ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በይፋ መለያየቱን ክለቡ አስታውቋል፡፡
አሠልጣኝ ዘሪሁን ከታዳጊ ቡድን ጀምሮ እስከዋናው ቡድን ለረጅም ዓመታት በአንድ ማሊያ ብቻ በመጫወት በድል አድራጊነት ደምቆ የዋንጫ ድሎችን መጎናጸፉን ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡
በተለይም ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት…
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለፓሪስ ኦሊምፒክ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ በማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክለው አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለውድድሩ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
አትሌት ቀነኒሳ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው÷ ለፓሪሱ ኦሊምፒክ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት አጠናቋል።
በዝግጀቱ አብረውት ለነበሩት የቡድን አሰልጣኞች፣ ለቡድኑ አባላት፣…