ስፓርት
ኢትዮጵያ በየትኛቹ ኦሊምፒኮች ተሳተፈች?
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ በኦሊምፒክ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ በታሪኳ በኦሊምፒክ መሳተፍ የጀመረችው ኦሊምፒክ ከተጀመረ ከ60 ዓመታት በኋላ አውስትራሊያ ባስተናገደችው 16ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ነው፡፡
በግሪክ አስተናጋጅነት በፈረንጆቹ 1986 የጀመረው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ውድድር አውስትራሊያ፣ ኦስትሪያ፣ ቡልጋሪያ፣ ቺሊ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ በወቅቱ አጠራር ታላቋ ብሪታንያ (አየርላንድን ጨምሮ)፣ ግሪክ፣ ሀንጋሪ፣ ጣልያን፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድና አሜሪካ ተሳትፈውበታል።…
Read More...
ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት የ5 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓሪስ እያስተናገደችው በሚገኘው 33ኛው ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት 5 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ከ15 ላይ ይካሄዳል፡፡
በዚሁ የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡
እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ከ47 ላይ በሚካሄደው…
አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለፍጻሜ አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡
አትሌት ሎሚ ከምድቧ 5ኛ እንዲሁም ሲምቦ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ነው ለፍጻሜው ያለፉት፡፡
የፍጻሜው ውድድር ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት 4 ሠዓት ከ10 ላይ እንደሚካሄድ የወጣው መርሐ-ግብር ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 ፓሪስ ኦሊምፒክ በተለያዩ ርቀቶች ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው ሦስት የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡
በዚህም መሠረት ቀን 5 ሠዓት ከ5 ላይ በሚካሄደው 3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ÷ አትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ ዓለማየሁ ይሳተፋሉ፡፡
እንዲሁም ምሽት 3 ሠዓት ከ35 ላይ በሚካሄደው 800 ሜትር…
የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ሽልማት ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር የእውቅና ሥነ-ስርዓት ተከናውኗል፡፡
በመርሐ-ግብሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የሥራ…
በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ፅጌ ዱጉማና ወርቅነሽ መሰለ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ፅጌ ዱጉማና ወርቅነሽ መሰለ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል፡፡
ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ 800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ተካሂዷል፡፡
በዚህም በምድብ ሁለት አትሌት ወርቅነሽ መሰለ 1፡58.07 እንዲሁም በምድብ ሶስት አትሌት ፅጌ…
በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬና መዲና ኢሳ ለፍፃሜ አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሎምፒክ 5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬና መዲና ኢሳ ለፍፃሜ አልፈዋል፡፡
ምሽት 1 ሠዓት ከ10 ላይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ተካሂዷል፡፡
በዚህም በምድብ አንድ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 14፡57፡84፣ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 14፡57፡97 በሆነ ሰዓት በመግባት ለፍፃሜው ማለፋቸውን…