Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አል ኢቲሃድ ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ተሳታፊው አል ኢቲሃድ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስን ከአሰልጣኝነት አሰናብቷል፡፡ የቀድሞ የቶተንሃም ሆትስፐር እና ወልቭስ አሰልጣኝ የነበሩት ሳንቶስ በሳዑዲ ፕሮ ሊግ ባሳዩት ደካማ እንቅስቃሴ ነው ከአሰልጣኝነት የተሰናበቱት፡፡ አሰልጣኙ ከተካሄዱ 12 ጨዋታዎች በ6ቱ ብቻ ያሸነፉ ሲሆን÷ አል ኢቲሃድ ባለፈው ሰኞ በእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ በኢራቁ ኤር ፎርስ ክለብ 2 ለ 0 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡ በዚህም አሰልጣኙ ከስምንት ወራት የሃላፊነት ቆይታ…
Read More...

የዋልያዎቹ ሁለት ተጫዋቾች ከስብስቡ ውጭ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ትናንት ዝግጅት መጀመሩ ይታወሳል። በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር። ጌታነህ ከበደ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን ተከትሎ ከስብስቡ ውጭ መሆኑ ሲረጋገጥ ሌሎቹ…

የአፍሪካ ህብረት በኒው ዮርክ ማራቶን አፍሪካን ላስጠሩ አትሌቶች ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ጽ/ቤት በኒው ዮርክ ማራቶን የአፍሪካን አህጉር ላስጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ኬንያውያን አትሌቶች ምስጋና አቅርቧል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ ÷በኒው ዮርክ ማራቶን ላሸነፉ የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ…

በሹዙ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቻይና ሹዙ በተካሄደ የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በወንዶች ምድብ አትሌት መልካ ደርቤ ርቀቱን 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡ በተመሳሳይ አትሌት ደራርቱ ሃይሉ በሴቶች ምድብ ርቀቱን 2 ሰዓት 27ደቂቃ ከ47 ሰከንድ በሆነ…

አትሌት ታምራት ቶላ የዘንድሮውን የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ታምራት ቶላ የዘንድሮውን የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር በአሸናፊነት አጠናቀቀ። አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዘንድሮውን የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች። በውድድሩ በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ 2:04:58 በሆነ ሰዓት በመግባት በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፤ ኬኒያዊው አትሌት…

10ኛው የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በውድድሩ በሴቶች ፍቅርተ ወረታ ከመቻል ስታሸንፍ፣ ጋዲሴ ሙሉ ከኦሮሚያ ፖሊስ እና የኔነሽ ጥላሁን ከኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ወጥተዋል፡፡ በወንዶች አንዱአለም በላይ ከፌደራል ፖሊስ ውድድሩን አንደኛ በመሆን አጠናቋል።…

አዲስ አበባ ስታዲየም የሳር ንጣፍ ሥራ በቅርቡ ለማስጀመር እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መመዘኛ መስፈርትን ተከትሎ እድሳት እየተደረገለት ያለው የአዲስ አበባ ስታዲየም የሳር ንጣፍ ሥራ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ። ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጨዋታዎችን በብቸኝነት ሲያስተናግድ የነበረው የአዲስ…