ስፓርት
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል።
በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሂደዋል።
በሳምንቱ ከተደረጉ ውድድሮች መካከል በስዊድን የተካሄደው የስቶኮልም ማራቶን ይገኝበታል።
በወንዶች አትሌት አሸናፊ ሞገስ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ÷ አትሌት ደራራ ሁሪሳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ጸጋዬ መኮንን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን በበላይነት ጨርሰዋል።
በሴቶች…
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከነማ መቻልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ27ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከነማ መቻልን 3 ለ 2 በማሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን አጠናክሯል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በተከናወነው መርሃ ግብር ሀብታሙ ታደሰ ሁለት ጎሎችን ለባህርዳር ከነማ ሲያስቆጥር የምንትስኖት አዳነ ቀሪዋን አንድ ጎል በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡
በረከት ደስታ እና…
አዲስ አበባ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሽዬቲቭ ሽልማት አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት ኢንሽዬቲቭ አሸናፊ ከሆኑ አስር የዓለማችን ከተሞች አንዷ ሆናለች።
ከአምስት አህጉራት 275 ተወዳድረው ነው 10 ከተሞች የውድድሩ አሽናፊ የሆኑት።
የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ አሸናፊዎቹ ሃገራት ፤ ኢትዮጲያን ጨምሮ ብራዚል ፣ ህንድ ፣ጣሊያን ፣ አልባኒያ ፣ ኒውዝላንድ…
የኢትዮጵያ ሜዳ ቴኒስ ስፖርተኞች ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት አስተናጋጅነት በሚዘጋጀው የሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ ስፖርተኞት ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገለት።
በኮንጎ ኪኒሻሳ እና በሩዋንዳ አዘጋጅነት በሚደረጉት የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና እና ዓለምአቀፍ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉት የወንዶች እና የሴቶች የስፖርት ልዑካን ቡድን ሽኝት እና የእራት ግብዣ…
ማንቼስተር ሲቲ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ሲቲ የከተማ ተቀናቃኙን ማንቼስተር ዩናይትድ በማሸነፍ የእንግሊዝ ኤፍ ኤፕ ካፕ ዋንጫን አሸንፏል።
11 ሰዓት ላይ በተካሄደው የማንቹሪያ ደርቢ የፍፃሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በጀርመናዊዉ አጥቂ ኤልካይ ጎንዶጋን ጎሎች 2 ለ 1 በማሸነፍ ዋንጫውን ከፍ አድርገዋል።
ሦስትዮሽ የዋንጫ ጉዟቸውን የቀጠሉት ስፔናዊው…
ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለገጣፎ ለገዳዲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቶጎዋዊው አጥቂ ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ በ16ኛው እና የአማካይ ተጫዋቹ ሀይደር ሸረፋ በ58ኛው ደቂቃ ለፈረሰኞቹ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።…
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጎፈሬ የትጥቅ አምራች ድርጀት ጋር አዲስ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
በአዲሱ ውል መሰረት ሀገር በቀሉ የትጥቅ አምራች ተቋም ጎፈሬ ለቀጣይ አራት ወራት ለኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች ለውድድር እና ለልምምድ የሚሆን የትጥቅ አቅርቦት ያደርጋል።
ጎፈሬ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ…