ስፓርት
በሴቶች 10 ሺህ ከ30 ደቂቃ በታች በማጠናቀቅ ኢትዮጵያ ታሪክ ሰራች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሚዛን ዓለም የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በአሸናፊነት አጠናቃለች፡፡
አትሌቷ በለንደን ’’ኮንቲነንታል ቱር’’ ላይ በተደረገው የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ከ30 ደቂቃ በታች በመግባት በታሪክ 12ኛዋ እንስት ሆናለች፡፡
በዚህ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሚዛን ዓለም 29 ደቂቃ 58 ሰከንድ 70ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ውጤት ነው ውድድሯን ያጠናቀቀችው፡፡
ይህም ታሪክ የማይረሳው የኢትዮጵያ ድል ነው ሲሉ የዓለም አትሌቲክስ እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን አሞካሽተውታል፡፡…
Read More...
አትሌት ጸሃይ ገመቹ በሕንድ ባንጋሉር የ10 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር አሸነፈች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጸሃይ ገመቹ በህንድ ባንጋሉር በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈች፡፡
አትሌት ጸሃይ ርቀቱን 31 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነው በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው፡፡
ከተማ አቀፍ የማርሻል አርት ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት የማርሻል አርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።
መርሐ ግብሩ “የማርሻል አርት ስፖርት ለከተማችን ሰላም እና ውጤታማ ትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት…
ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ።
2006 ዓ.ም የተመሰረተው ሀምበሪቾ ዱራሜ ከአራት ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ተቀላቅሎ ሲሳተፍ መቆየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።
ያለፉትን ዓመታት በሊጉ ሲሳተፍ ቆይቶ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን…
አቶ ውብሸት ደሳለኝ የብሄራዊ ቡድኑ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)አቶ ውብሸት ደሳለኝ የዋሊያዎቹ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በጊዜያዊነት እንዲመሩ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና አሰልጣኝ እና ምክትል አልጣኝነት መሾሙ ይታወሳል፡፡
የግብ…
የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ እየመራ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀዋሳ ከተማ ነጥብ ጥሏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከእረፍት መልስ በቸርነት ጉግሳ ጎል መምራት ቢችልም ተባረክ ሄፋሞ በፍፁም ቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ ሀዋሳን…
ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የዲ ኤስ ቲቪ ቀጥታ ስርጭት ሽፋን አያገኙም – ሊግ ኩባንያው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ25ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች የዲ ኤስ ቲቪ ቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማያገኙ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ፡፡
ማህበሩ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ መሆኑን እና ውድድሩ በቀጥታ የሱፐር ስፖርት ሽፋን እያገኘ…