Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮ- ኤሌክትሪክ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወረደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለገጣፎ ለገዳዲን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መውረዱን ያረጋገጠ ሁለተኛ ክለብ ሆኗል። ኢትዮ- ኤሌክትሪክ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዲስ መልክ መደረግ ከጀመረበት 1990 አንስቶ ሁለት ጊዜ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2010 ላይ ከሊጉ ከወረደ በኋላ ዘንድሮ አድጎ የነበረ ቢሆንም አምስት ጨዋታዎች እየቀሩት ለገጣፎ ለገዳዲን ተከትሎ በመጣበት ዓመት መውረዱ ተረጋግጧል። በዛሬው መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል ጋር ባደረገው ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይቷል።
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ከፋሲል ከነማ ጋር የተጫወተው ሲዳማ ቡና በደስታ ደሙ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በተከታታይ 3 ጨዋታዎችን ማሸነፍ የቻለው ሲዳማ ቡና ከወራጅ ቀጠና ስጋት መውጣት የቻለ ሲሆን÷ ነጥቡን 33…

በሴቶች 10 ሺህ ከ30 ደቂቃ በታች በማጠናቀቅ ኢትዮጵያ ታሪክ ሰራች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሚዛን ዓለም የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በአሸናፊነት አጠናቃለች፡፡ አትሌቷ በለንደን ’’ኮንቲነንታል ቱር’’ ላይ በተደረገው የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ከ30 ደቂቃ በታች በመግባት በታሪክ 12ኛዋ እንስት ሆናለች፡፡ በዚህ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሚዛን ዓለም 29 ደቂቃ 58 ሰከንድ…

አትሌት ጸሃይ ገመቹ በሕንድ ባንጋሉር የ10 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጸሃይ ገመቹ በህንድ ባንጋሉር በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈች፡፡ አትሌት ጸሃይ ርቀቱን 31 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነው በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው፡፡

ከተማ አቀፍ የማርሻል አርት ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት የማርሻል አርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል። መርሐ ግብሩ “የማርሻል አርት ስፖርት ለከተማችን ሰላም እና ውጤታማ ትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት…

ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ። 2006 ዓ.ም የተመሰረተው ሀምበሪቾ ዱራሜ ከአራት ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን ተቀላቅሎ ሲሳተፍ መቆየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል። ያለፉትን ዓመታት በሊጉ ሲሳተፍ ቆይቶ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን…

አቶ ውብሸት ደሳለኝ የብሄራዊ ቡድኑ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)አቶ ውብሸት ደሳለኝ የዋሊያዎቹ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በጊዜያዊነት እንዲመሩ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና አሰልጣኝ እና ምክትል አልጣኝነት መሾሙ ይታወሳል፡፡ የግብ…