Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የዕለተ ሰኞ የውጭ አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች

ሞሮኮ ከቻን ውድድር ራሷን ማግለሏ ተሰምቷል፤ይህን ተከትሎም በቻን የምድብ ማጣሪያ መርሐ ግብር ከሞሮኮ ጋር ጨዋታ የነበራት ሱዳን በፎርፌ አሸንፋለች፡፡   የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት አቅም አለን ሲል ፈረንሳዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ተከላካይ ራፋይል ቫራን ተናግሯል፡፡   ቫራን ይህን ያለው በማንቹሪያ ደርቢ ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን በማሸነፍ ከመሪዎቹ አርሴናል እና ማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበቡን ተከትሎ ነው፡፡   ከአርሴናል ጋር መዋዳደር ከባድ ነገር ሊሆን…
Read More...

በሂውስተን ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች  አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በተካሄደው የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጸታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በሂውስተን የወንዶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ልዑል ገብረ ስላሴ አሸንፏል፡፡ አትሌት ልዑል ርቀቱን 1፡00፡34 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈው፡፡ በሴቶች ግማሽ ማራቶን ምድብ ደግሞ አትሌት…

በስፔን በተካሄደ የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው አሸነፈች፡፡ ውድድሩን 29 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ በመግባት ነው አትሌት የዓለምዘርፍ ያሸነፈችው፡፡

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ዛሬ ወደ ውድድር ትመለሳለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የረጅም ርቀት ሯጯ ጥሩነሽ ዲባባ ከአራት ዓመታት በኋላ ዛሬ በአሜሪካ በሚካሄደው የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ወደ ውድድር ትመለሳለች። የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ እና የአምስት ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው አትሌት ጥሩነሽ ባለፉት አራት ዓመት ምንም አይነት ውድድር አድርጋ አታውቅም። ዛሬ ለ22ኛ ጊዜ…

በሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ማለዳ በሕንድ በተካሄደው የሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ። በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 8ኛ ተከታትለው በመግባት በበላይት አጠናቀዋል፡፡ በውድድሩ አትሌት አንቺዓለም ሃይማኖት 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር…

በማንችስተር ደርቢ ዩናይትድ ሲቲን 2 ለ1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ የማንችስተር ደርቢ ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል። የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ማርከስ ራሽፎርድ እና ፈርናንዴዝ ሲያስቆጥሩ የማንችስተር ሲቲን ግብ ግሪሊሽ አስቆጥሯል። ማንችስተር ዩናይትድ በተከታታይ…

ኢትዮጵያ ከሞዛምቢክ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ ያለምንም ግብ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ7ኛው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒየን ሺፕ ቻን ውድድር የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋን ከሞዛምቢክ ጋር ያደረገችው ኢትዮጵያ ጨዋታዋን ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት አጠናቃለች። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቻ መውጣቱን ተከትሎ አንድ ነጥብ በመያዝ በምድቡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 7ኛው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒየንሺፕ ውድድር…