ስፓርት
ፊፋ የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ስላሳየው ያልተገባ ባህሪ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ባለፈው ወር በኳታር በተካሄደው የአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ፥ የ2018 ዓለም ዋንጫ አሸናፊዋን ፈረንሳይን በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፋ ዋንጫውን ለሶስተኛ ጊዜ ባነሳችው በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን "ያልተገባ ባህሪ" ላይ የዲሲፕሊን ሂደቶችን ከፍቻለሁ ብሏል።
በፍፃሜ ጨዋታው መጨረሻ ግብ ጠባቂው ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ በምርጥ በረኛነት ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ያልተገባ ምልክት ማሳየቱ የተገለፀ ሲሆን፤ ከመቀረጹ በፊት በመልበሻ ክፍል ውስጥ በፈረንሳዊው ኮከብ ኪሊያን…
Read More...
ኢትዮጵያ የፊታችን እሑድ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ጉባኤን ታስተናግዳለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተካለሉበት የአትሌቲክስ ሪጅን ጉባኤ የፊታችን እሑድ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይካሄዳል፡፡
በጉባኤው የሪጅኑ ፕሬዚዳንት፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫና በሪጅኑ የኮንፌዴሬሽን ኦፎ አፍሪካ አትሌቲክስ ካውንስል አባላት ውክልና…
ብሄራዊ ቡድኑ ከሞዛምቢክ ጋር ለመጫዎት ዝግጁ ነው – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት ከሞዛምቢክ ጋር ለሚደርገው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ፡፡
በነገው ዕለት የሚካሄደውን ጨዋታ አስመልክቶ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ መስኡድ መሐመድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ በመግለጫቸውም÷ ብሄራዊ ቡድኑ በሀገር ቤት ዝግጅት ሲያደርግ…
ዕለታዊ አጫጭር የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎች
ቼልሲ ከ 17 ዓመት በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ በፉልሃም 2 ለ 1 ተሸንፏል፤የትላንት ምሽቱን ውጤት ተከትሎም አሰልጣኝ ግራም ፖተርስ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል፡፡
በጨዋታው የተሰለፈው አዲሱ ፈራሚ ዣኦ ፊሊክስ ለፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን ቢያደርግም ሜዳ ውስጥ በፈጸመው ጥፋት በ58ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ2022 የፊፋ ምርጥ የወንድ…
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ማራቶን ይሳተፋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች እንደሚሳተፉ የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡
በወንዶች ምድብ ሌሊሳ ዴሲሳ፣ሹራ ቂጣታ፣ አንዳምላክ በልሁ ፣ አንዱዓለም በላይ እንዲሁም ሂርጳሳ ነጋሳ በውድድሩ ይካፈላሉ፡፡
በሴቶቹ ደግሞ የዓለም የማራቶን ሻምፒዮኗ ጎይተይቶም ገብረስላሴ እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር አልጄሪያ ገብቷል
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ውድድር አስተናጋጅ በሆነችው አልጄርያ በሰላም ገብቷል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ አልጀርስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአልጀርያ ባህላዊ ሙዚቃ የታጀበ አቀባበል ተደርጎለታል።
ዋልያዎቹ በቻን ውድድር በምድብ አንድ ከአዘጋጇ አልጄሪያ እንዲሁም ሞዛምቢክ እና ሊቢያ ጋር…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አልጄሪያ አቀና
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚካሔደው ሰባተኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና (ቻን) የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አልጀሪያ አቀና፡፡
ውድድሩ ከነገ በስቲያ ይጀመራል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ቅድመ ዝግጅት አድርጓል።
ዋልያዎቹ በቻን ውድድር በምድብ አንድ ከአዘጋጇ…