Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞሮኮ አቻው ጋር ምሽት 1ሰዓት የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ቡድኑ ከሞሮኮ ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ራባት መሐመድ ስድስተኛ እግር ኳስ አካዳሚ ተገኝቷል። ጨዋታውም ምሽት 1 ሰዓት እንደሚጀመር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ለቻን ዝግጅት ሞሮኮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከሞሮኮ አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የመጀመርያ የወዳጅነት ጨዋታው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
Read More...

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ልትመለስ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ ጥር 15 በሚካሄደው 22ኛው የአራምኮ ሂዩስተን የግማሽ ማራቶን ውድድር የርቀቱ የምንጊዜም ታላቅ ሯጮች መካከል አንዷ የሆነችው ጥሩነሽ ዲባባ ትሳተፋለች፡፡ የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ እና የአምስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊዋ አትሌት ጥሩነሸ ዲባባ በግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ የግሏ…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሞሮኮ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር ዝግጅት ወደ ሞሮኮ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ወደ ግብፅ ካይሮ በረራ ያደረገ ሲሆን ፥ ቡድኑ ከደቂቃዎች በፊት በሰላም ካይሮ መድረሱ ታውቋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ለትንሽ ደቂቃዎች በካይሮ አየር ማረፍያ ቆይታ ካደረገ በኋላም ወደ ሞሮኮ ጉዞውን የሚቀጥል መሆኑን…

በፓን አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ ትምህርት ቤቶች ታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 ( ኤፍ ቢ ሲ) ገዳ ሮበሌ አንደኛ ደረጃ እና አዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፓን አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚወዳደሩ ታውቋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ከ16 አመት በታች የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ የማጣሪያ ውድድር ዛሬ ተጠናቋል፡፡…

የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን የተማሪዎች  የእግር ኳስ ውድድር  ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን የተማሪዎች  የእግር ኳስ ውድድር   በአዳማ ከተማ ተጀምሯል፡፡ በማስጀመሪያ መርሃግብሩ  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሃፊ ባህሩ ጥላሁን ÷ የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን   ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት አንፃር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡ የባህልና ስፖርት…

40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱሉልታ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ተጠናቋል፡፡ በማጠናቀቂያ መርሐ ግበሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ፕሬዚዳንት ጄነራል ጃክሰን ትዊ…

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮን ሆነች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለምሻምፒዮና የ10ሺህ ሜትር አሸናፊዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮናን አሸነፈች፡፡ ውድድሩ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ለ40ኛ ጊዜ በሱሉልታ ሲካሄድ የአለም ቻምፒዮኖች፣ የኦሊምፒክ ኮከቦችና ሌሎች ጠንካራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡ የጃንሜዳን የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር…