Fana: At a Speed of Life!

ማዕከላዊ እዝ ስኬታማ ግዳጁን በብቃት እያስቀጠለ ነው- ጄኔራል አበባው ታደሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማዕከላዊ እዝ እየፈፀመ የመጣውን ስኬታማ ግዳጅ በላቀ ብቃት እያስቀጠለ ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ገለጹ፡፡

ጀኔራል አበባው ከማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በቀጠናው የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው ሸኔ ሕዝብን ሲዘርፍ እና ሲያሰቃይ እንደነበር አስታውሰው÷ ዕዙ ይህን ቡድን ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ በሚያስችል አግባብ ተልዕኮውን እየፈፀመ መሆኑን ጄኔራል አበባ ተናግረዋል፡፡

እንደ እዝ በይበልጥ በውጤት የሚለካ ስራ በዘላቂነት መስራት እንደጠበቅም አስገንዝበዋል፡፡

እየተከናወኑ ያሉ መልካም ሥራዎችን ለማስቀጠል የማያቋርጥ የስነ-ልቦና ስራዎችን በየደረጃው ያለ የእዙ አመራር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባውም ነው ያሳሰቡት።

የእዙ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ በበኩላቸው በአነስተኛ ኃይል የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ ክፍሎችን የመፍጠሩ ሂደት በትኩረት እየተሠራበት ነው ብለዋል፡፡

የእዙ የሰራዊት አባላት በራስ መተማመን ያለውና የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በላቀ ውጤት እየፈፀመ ይገኛል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.