ስፓርት
ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምድብ አራት የተደለደሉት ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ያረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቋል፡፡
10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደረጉት ዴንማርክ እና ቱኒዚያ አቻ በሆነ ውጤት መለያየታቸውን ተከትሎ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡
በዚህም የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከተጀመረ ጀምሮ ያለምንም ጎል የተጠናቀቀ የመጀመሪያው ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
22ኛው የዓለም ዋንጫ በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሔደ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦…
Read More...
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ሲዳማ ቡና መቻልን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ÷ ጎሎቹን ፍሬው ሰለሞን በ17ኛው እና ሙሉዓለም መስፍን በ75ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዋሳ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ጎሎቹንም÷…
አርጀንቲና ባልተጠበቀችው ሳዑዲ የዓለም ዋንጫውን በሽንፈት ጀምራዋለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ሶስተኛ ቀን ውሎ ሳዑዲ ዓረቢያ ያልተጠበቀ ድል አስመዝግባለች።
ከደቡብ አሜሪካዋ አርጀንቲና ጋር የተጫወተችው ሳዑዲ ከመመራት ተነስታ 2 ለ 1 አሸንፋለች።
በጨዋታው ሊዮኔል መሲ በ10ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠረው ጎል አርጀንቲና 1 ለ 0 መምራት ብትችልም ሳዑዲዎች በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታውን…
በሦስተኛው ቀን የዓለም ዋንጫ ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሦስተኛ ቀኑን በያዘው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ፡፡
በምድብ ሦስት የተደለደለችው አርጀንቲና ቀን 7 ሰአት ላይ ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ትጫወታለች፡፡
ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው በሆነው የዓለም ዋንጫ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር በድል ለመመለስ ዛሬ አንድ ብሎ ይጀምራል።
በዚሁ ምድብ የደለደሉት ሜክሲኮ እና…
በአለም ዋንጫ ሴኔጋል በኔዘርላንድስ ተሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው ቀን የኳታር የዓለም ዋንጫ ጨዋታ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 ተሸንፋለች፡፡
የኔዘርላንድስን የማሸነፊያ ጎሎች የፒኤስቪው አጥቂ ኮዲ ባክፖ እና የአያክሱ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ዴቪ ኬላሰን አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው የተሳኩ ሙከራዎችን ማድረግ የቻለችው ሴኔጋል ኔዘርላንድስን መፈተን ብትችልም…
ሊግ ኩባንያው በ8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ በቀረቡ የሥነ ምግባር ጉዳዮችላይ ውሳኔ አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ በቀረቡ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ እና ሶስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 23 ጎሎች በተቆጥረዋል።
በሳምንቱ…
በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ሦስት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የሁለተኛ ቀን ውሎ ዛሬ ሦስት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡
በምድብ ሁለት የሚገኙት እንግሊዝ እና ኢራን ከቀትር በኋላ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በጉዳት ሳዲዮ ማኔን ያጣችው ሴኔጋል ከኔዘርላንድስ ጋር ምሽት 1 ሰዓት ላይ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች።…