Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በወንዶች አትሌት አቤ ጋሻው ለሦስተኛ ጊዜ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በወንዶች ከአማራ ማረሚያ ቤት አትሌት አቤ ጋሻው አሸንፏል፡፡ አትሌት አቤ ጋሻው የዘንድሮውን ሲያሸንፍ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግሯል፡፡ አትሌት ኃይለማርያም አማረ ከፌደራል ማረሚያ ሁለተኛ እና አትሌት ገመቹ ዲዳ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አጠናቀዋል፡፡ በተመሳሳይ በሴቶች የተካሔደውን ውድድር ከኦሮሚያ ደን ጥበቃ ኢንተርፕራይዝ አትሌት ትዕግስት ከተማ አንደኛ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መስታወት ፍቅሩ ሁለተኛ እና…
Read More...

የዓለም ዋንጫ ዛሬ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቀው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ በኳታር ይጀመራል። የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ 60 ሺህ ገደማ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ባለው አል በይት ስታዲየም ይካሔዳል፡፡ በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ የውድድሩ ሳውንድ ትራክ ተብሎ በፊፋ እውቅና የተሰጠው "ሃያ ሃያ" (አብሮነት ይሻላል) የሚለው ሙዚቃ…

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂ አትሌቶችን ጨምሮ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በሩጫው የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ÷ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ፣ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናኒሴ ጫሊ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ…

በፕሪሚየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያይተዋል፡፡ በ8ኛ ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ በዚህም 10 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡…

በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሄደዋል። 10 ሰአት ላይ በተደረገ የመጀመሪያው ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ፉአድ ፈረጃ፣ ፍፁም ጥላሁን እና ያሬድ ባየህ የባሕርዳርን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የኢትዮጵያ ቡና ጎል ሮቤል ተክለሚካኤል አስቆጥሯል፡፡ ባሕርዳር ከተማ…

ሊግ ኩባንያው የቴሌቪዥን መብት የመጀመሪያ ክፍያን ለክለቦች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ2015 ዓ.ም የቴሌቪዥን መብት የመጀመሪያ ክፍያን ለክለቦች መፈጸሙን አስታውቋል፡፡ በዚህ መሰረትም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሳታፊ 16 ክለቦች እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ከሊግ ኩባንያው ማግኘታቸው ተመላክቷል፡፡ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ…

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል። በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተከናውነዋል። 10 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል። የድል ጎሎቹን ዮናታን ኤሊያስ እና ቃል ኪዳን ዘላለም ሲያስቆጥሩ ቦና ዓሊ ደግሞ የአዳማ ከተማን ማስተዛዘኛ ጎል…