ስፓርት
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት በጋራ ስምምነት መለያየታቸው ተገለጸ፡፡
ተሰናባቹ አሰልጣኝ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት መርተዋል፡፡
ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ አሰልጣኝ ውበቱ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ የአሰልጣኙን መልቀቂያ በመቀበሉ በጋራ ስምምነት ተለያይተዋል።
የኢትዮጵያ…
Read More...
የጣና ሞገዶቹ ድሬዳዋ ከተማን ረቱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሣምንት ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡
ባሕዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 9፡00 ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡
በዚህም ሀብታሙ ታደሠ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች እና ዱሬሳ ሹቢሳ…
በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ ከሀድያ ሆሳዕናን ጋር የተጫወቱት ድሬዳዋ ከተማ ከመመራት ተነስተው ከዕረፍት መልስ ቢኒያም ጌታቸው እና አቤል አሰበ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም በረሀማዎቹ ነጥባቸውን 24 በማድረስ…
አስራት አባተ የድሬዳዋ ከተማ ዋና አስልጣኝ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሰልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይ ጋር የተለያየው ድሬዳዋ ከተማ የዋልያዎቹ ምክትል አሰልጣኝ የነበረው አስራት አባተን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ፡፡
በረሐማዎቹ በፕሪሚየርሊጉ በ21 ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ዋሊያዎቹ በአሜሪካ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሐምሌ ወር በአሜሪካ የጉብኝት ጉዞ ሊያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡
በዚህም ቡድኑ በፈረንጆቹ ሐምሌ 8 ቀን 2023 ዋሺንግተን እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በቆይታውም ከካሪቢያን ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ጨዋታ እንደሚያደርግ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡…
በፕሪሚየር ሊጉ ሃዋሳ ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ18ኛ ሣምንት ጨዋታ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በዚህ መሰረትም አዳማ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡
በጨዋታውም ሃዋሳ ከተማ ተጋጣሚውን አዳማ ከተማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል፡፡…
ኢትዮጵያ ቡና እና ባሕርዳር ከተማ ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቡና እና ባሕርዳር ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ፡፡
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሣምንት ጨዋታ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በዚህም 9፡00 ላይ በተካሔደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ለቡና የማሸነፊያዋን ጎል ብሩክ በየነ…