Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በሻምፒዮናው የመጠናቀቂያ ዕለት ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (2014) በዛሬው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቂያ ዕለት በወንዶች 5 ሺህ ሜትር እና በሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም። በወንዶች 5 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያው ወደ ኖርዌይ ሄዷል። በውድድሩ ዩሚፍ ቀጀልቻ 8ኛ፣ ሰለሞን ባረጋ 12ኛ እና ሙክታር ኢድሪስ 13ኛ ሆነው አጠናቀዋል። የኬንያ እና ኡጋንዳ አትሌቶች ተከታትለው ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል። በሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ድርቤ ወልተጂ አራተኛ ሆና አጠናቃለች።
Read More...

በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000 ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ18ኛው የኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000 ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይደረጋል። ለሊት 10:05 በሚደረገው የወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ ውድድር ላይ ሶስት ኢትዮጵያውን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ሙክታር ኢድሪስ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ የሚሳተፉ ይሆናል። በተመሳሳይ ለሊት 10:35…

በኦሪገን ኢትዮጵያ በጉዳፍ ፀጋይ 4ኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶቾ 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ለኢትዮጵያ 4ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች። ዳዊት ስዩም ሶስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ውድድሩን ለተሰንበት ግደይ አምስተኛ በመውጣት አጠናቃለች። በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ግሩም የቡድን ሩጫ አሳይተዋል።…

የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይካሄዳል፡፡ 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአሜሪካ ኦሪገን መካሄዱን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ዛሬ ሌሊት 10፡25 የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡ በሩጫ ውድድሩ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉት አትሌቶች…

በሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የሴቶች 800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ሌሊት 10 ሰዓት ከ35 ላይ ይካሄዳል፡፡ በውድድሩ አትሌት ደርቤ ወልተጂ፣ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ እና አትሌት ሀብታም አለሙ ይሳተፋሉ፡፡ ትናንት በተካሄደው የሩብ ፍጻሜ ውድድር÷ ከምድብ አንድ አትሌት ደርቤ ወልተጂ…

ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ የካፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ እና የአሁኑ የባየር ሙኒክ አዲስ ፈራሚ ሳዲዮ ማኔ የካፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡ ሳዲዮ ማኔ በክለቡ ሊቨርፑል ማራኪ የውድድር ዓመት ከማሳለፉ በተጨማሪ÷ ሀገሩ ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን እንድትሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጉ ነው የካፍ የ2022 ምርጥ…

በወንዶች 5 ሺህ ሜትርና በሴቶች 800 ሜትር ስድስት ኢትዮጵያውያን ማጣሪያን አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወንዶች 5 ሺህ ሜትርና በሴቶች 800 ሜትር ስድስት ኢትዮጵያውያን ማጣሪያን አለፉ። የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ከምድብ 1 አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ13:24.44 በሆነ ሰዓት 3ኛ ሆኖ በመግባት ቀጥታ ሲያልፍ አትሌት በ13:24.77 በሆነ ሰዓት 7ኛ የገባው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ ማጣሪያውን አላለፈም። ከምድብ 2…