ስፓርት
ሉሲዎቹ የዛንዚባር አቻቸውን 5 ለ 0 አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 204 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ውድድር ዛንዚባርን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን (ሉሲዎች) 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡
የማሸነፊያ ጎሎችን አረጋሽ ካልሳ የመሪነቱን ጎል ስታስቆጥር ሎዛ አበራ እና ቅድስት ዘለቀ ሁለት ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል፡፡
የምስራቅና የመካከለኛው የአፍሪካ የሴቶች ሴካፋ ሻምፒዮና ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን ዛንዚባርን በሰፊ ውጤት በማሸነፍ በመድረኩ ጥሩ አጀማመር ማሳየት ችሏል፡፡
Read More...
የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ከእረፍት መልስ የፊታችን ሰኔ 7 ቀን ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ከእረፍት መልስ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የበላይነት የሚከናወነው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ውድድር ከ22ኛ ሳምንት ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጅ…
ሉሲዎቹ ነገ ከዛንዚባር አቻቸው ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ነገ 7 ሰዓት ከዛንዚባር አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል ፡፡
በሴካፋ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ስፍራው የደረሰው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ላይ የመጀመሪያ ልምምዱን አከናውኗል።
በምድብ ሁለት ከታንዛኒያ፣ ዛንዚባር እና ደቡብ ሱዳን ጋር የተደለደለው ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን ነገ 7 ሰዓት…
ካሪም ቤንዜማ የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር አጥቂ ካሪም ቤንዜማ የውድድር አመቱ የቻምፒየንስ ሊጉ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡
ፈረንሳዊው አጥቂ ክለቡ ሪያል ማድሪድ ለ14ኛ ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን በማንሳት ክብረ ወሰኑን ይዞ እንዲቆይ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።
በመድረኩም 15 ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ…
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዋልያዎቹ ስብስብ አምስት ተጫዋቾችን ቀነሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዋልያዎቹ ስብስብ አምስት ተጨዋቾችን መቀነሳቸው ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ከማላዊ እና ግብፅ ጋር ለማድረግ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከጠሯቸው 28 ተጨዋቾች አምስት ተጨዋቾችን መቀነሳቸው ታውቋል፡፡
አሰልጣኙ ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር…
ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውጤታማነቷን ለማሳደግ የውድድሮች አይነቶችን ማስፋት አለባት – አትሌት ፖል ቴርጋት
አዲስ አበባ፣ግንቦት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውጤታማነቷን ለማሳደግ የምትሳተፍባቸውን የውድድR አይነቶች ማስፋት አለባት ሲል ታዋቂው ኬንያዊ አትሌት ፖል ቴርጋት ተናገረ።
ከአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ብርቱ ተፎካካሪዎች መካከል የነበረው ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት በሐዋሳ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ወጣቶች የኦሊምፒክ…
የመጀመሪያው የወጣቶች ሃገር አቀፍ ኦሊምፒክ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የወጣቶች ሃገር አቀፍ የኦሊምፒክ ጨዋታ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተጀምሯል።
በጨዋታው ከአማራ ክልል ውጭ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ስፖርተኞች ተሳታፊዎች መሆናቸው ተገልጿል።
በመክፈቻ ስነ ስርአቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ…