Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የአማራ ክልል ለቅድመ ዝግጅት ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቅድመ ዝግጅት የአማራ ክልል ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በደብዳቤ እንዳስታወቀው÷ 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በባህርዳር ከተማ እንዲካሄድ ውሳኔ በማሳለፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል፡፡ ነገር ግን የካቲት 21 ቀን 2014ዓ.ም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባደረገው ስበሰባ አንዳንድ ክለቦች እና ክልሎች ያቀረቡትን የበጀት ወጪ መጠንን ቁሳቁስ ለማጓጓዝ…
Read More...

በአትሌቲክስ ሻምፒዮና መከላከያና ኢትዮ ኤሌትሪክ ስፖርት ክለቦች የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አገኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና መከላከያና ኢትዮ ኤሌትሪክ ስፖርት ክለቦች የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡ ዛሬ በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ስታዲየም በተካሄደው ውድድር÷ በሴቶች አሎሎ ውርወራ የመከላከያዋ አትሌት ዙርጋ ኡስማን 13 ነጥብ 56 ሜትር በመወርወር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።…

አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የዓለም የ10 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ሰበረች

አዲ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን በተካሄደ የአለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የዓለም የ10 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን በመስበር ጭምር ውድድሩን በበላይነት አጠናቀቀች፡፡ ከዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ አትሌት ያለምዘርፍ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን 29:14 በሆነ ጊዜ…

አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሪከርድ በማሻሻል ጭምር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ የቦታውን ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸንፏል፡፡ አትሌቱ 28:34 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው የቦታውን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል መሸነፍ የቻለው፡፡ በተመሳሳይ በቱርክ ኢስታንቡል በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፀሐይ ገመቹ…

ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ በወንዶች የሮም ማራቶን አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሮም የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ አዲስ ክብረ ወስን በማስመዝገብ አሸነፈ፡፡ አትሌቱ 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት አዲስ ክብረ ወሰን የሰበረ ሲሆን፥ ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪፕቶ በ2009 ያስመዘገበውን ሪከርድ በመሰበር ነው ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀው። አትሌት ታደሰ ማሞ ውድድሩን…

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን መቀላቀሉን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ሊግ ሲጫወት የቆየው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን መቀላቀሉን አረጋግጧል፡፡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ጌዲዮ ዲላን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዳልካቸው ይልቃል እና አቤል ሀብታሙ ባሰቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡ የዛሬ ረፋዱን ውጤት ተከትሎም ኢትዮ ኤሌክትሪክ…

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ያከናውናል። በአሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል የሚመራው ብሄራዊ ቡድኑ ምሽት 12 ሰዓት ለሚካሄደው የመልስ ጨዋታ ወደ አክራ በማቅናት ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም…