ስፓርት
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ሀገር ቤት ተመልሷል
አዲስ አበባ፣ሰኔ 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር መልስ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።
ብሄራዊ ቡድኑ በሳምንታት ቆይታው በማላዊ 2 ለ 1 ቢሸነፍም ግብጽን 2 ለ 0 በማሸነፍ በግብ ክፍያ በልጦ የምድቡ አናት ላይ መቀመጥ ችሏል።
ዋሊያዎቹ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሳቸው በፊት በማላዊዉ ካሙዙ ኤርፖርት የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ያዘጋጀላቸውን የድል ኬክ በመቁረስ ጉዟቸውን ያደረጉ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።
ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ…
Read More...
በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሠናክል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሞሪሺየስ እተካሄደ በሚገኘው የ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ዛሬ በተደረገው የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ወንዶች ውድድር አትሌት ሃይለማሪያም አማረ እና አትሌት ታደሰ ታከለ 1ኛ እና ሁለተኛ በመሆን የወርቅና የብር ሜዳልያ ለአገራቸው ማስገኘታቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው…
በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅና የብር ሜዳልያዎች አገኘች
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የወርቅና የብር ሜዳልያዎች አገኘች።
ሜዳልያዎቹ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የተገኘ ነው።
በውድድሩ አትሌት ሞገስ ጥኡማይ እና አትሌት ጭምዴሳ ደበላ ተከታትለው በመግባት ለሃገራቸው ሜዳልያዎቹን ማስገኘታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደራሽን መረጃ ያመላክታል።…
22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሪሺየስ የሚካሄደው 22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጀምሯል።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 28 ሴት እና 26 ወንድ በድምሩ 54 አትሌቶችን የምታሳትፍ ሲሆን÷በመክፈቻው ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የማጣሪያ ውድድሮች ይካፈላሉ።
በ100 ሜትር ሴቶች ራሔል ተስፋዬ እና ያብስራ ጃርሶ፣ በ400 ሜትር ሴቶች ፅጌ…
በሴቶች የሴካፋ ዋንጫ ሉሲዎቹ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሴቶች (ሴካፋ) ዋንጫ ሉሲዎቹ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡
ዛሬ በተደረገ የሴቶች የሴካፋ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ሉሲዎቹ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 0 ረተዋል፡፡
በጨዋታው አረጋሽ ካልሳ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሃት - ትሪክ ስትሰራ ሎዛ አበራ አንደኛውን ጎል ማስቆጠር ችላለች፡፡…
ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በማላዊ ተሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ ጋር የተጫወቱት ዋልያዎቹ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል፡፡
በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋባዲኖ ማህዶ የማላዊን ሁለት ጎሎች በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር የኢትዮጵያን ብቸኛ ጎል አቡበከር ናስር በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
ዋልያዎቹ ከዕረፍት…
አርጀንቲናዊው ኮከብ ካርሎስ ቴቬዝ ከእግር ኳስ ዓለም መገለሉን አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ካርሎስ ቴቬዝ ከእግር ዓለም መገለሉን ይፋ አደረገ።
የቀድሞው የማንቼስተር ዩናይትድ፣ ማንቼስተር ሲቲ እና ጁቬንቱስ ኮከብ በ38 አመቱ እግር ኳስ ማቆሙን በይፋ አስታውቋል።
“በአወዛጋቢ” የእግር ኳስ ህይወቱ የሚታወቀው ቴቬዝ አሳዳጊ አባቱን ባለፈው አመት በኮቪድ ሳቢያ ማጣቱ…