Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ተጠባቂው የለንደን ደርቢ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ቼልሲ ከ አርሰናል የሚያደርጉት የለንደን ደርቢ ይጠበቃል። የከተማ ተቀናቃኞቹ አርሰናል እና ቼልሲ በካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በስታምፎርድ ብሪጅ ምሽት 5፡00 ላይ ያደርጋሉ። በአዲስ አሰልጣኝ እየተመሩ ወደ ጨዋታው የሚገቡት ቼልሲዎች በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት የከተማ ተቀናቃኛቸውን ይፋለማሉ። እንዲሁም ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ተጉዞ ባካሄዳቸው ያለፉት 6 ጨዋታዎች ምንም ዓይነት ሽንፈት ያላስተናገደው አርሰናል ከሰማያዊዎቹ ከባድ…
Read More...

በዓለም የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ፍሎሪዳ በተካሄደው 46ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ዛሬ ጠዋት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገው የአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ…

የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ’ የሩጫ ውድድር በደብረብርሃን ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ 2018’ የሩጫ ውድድር በደብረብርሃን ከተማ ተካሂዷል። ውድድሩ ከዚህ በፊት በአራት የተለያዩ ከተሞች ይደረግ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ደብረብርሃን እና ሀረርን በማካተት በስድስት ከተሞች ይደረጋል። በስፖርት ቱሪዝምን ማስተዋወቅ…

ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 አሸንፏል። ቀን 10፡00 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቅቋል። በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ዘላለም አባተ እና አቡበከር አዳሙ ከመረብ ጋር አገናኝተዋል።…

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል። ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ነው ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው ጨዋታቸውን ያጠናቀቁት። ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም…

ባሕር ዳር ከተማ መቻልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ14ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ቀን 7 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የባሕር ዳር ከተማን ግቦች ፍቅረሚካኤል ዓለሙ እና ግርማ ዲሳሳ ሲያስቆጥሩ መሐመድ አበራ የመቻልን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል። የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ከቀኑ…

በአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች አልጄሪያ ከናይጄሪያ እንዲሁም ግብፅ ከኮትዲቯር ይገናኛሉ። ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ በውድድሩ ጠንካራ አቋማቸውን በማስመልከት የምድብ ጨዋታቸውን ሙሉ በሙሉ ያሸነፉት አልጄሪያ እና ናይጄሪያ ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ይፋለማሉ። የዚህ…