ስፓርት
ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው የማንቹርያን ደርቢ ጨዋታ የቀያዮቹን ግቦች ብሪያን ምቡሞ እና ፓትሪክ ዶርጉ ከመረብ አሳርፈዋል።
በጨዋታው ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ብልጫ ወስዶ የተጫወተ ሲሆን÷ ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ ደካማ የማጥቃት እንቅስቃሴ አድርጓል።
በዚህ 198ኛው የማንቼስተር ደርቢ ጨዋታ በዩናይትዶች አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ዩናይትድ…
Read More...
መቻል አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቻል አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የመቻልን ግቦች ቸርነት ጉግሳ በፍጹም ቅጣት ምት እና ቻርለስ ሙሲጌ በጨዋታ አስቆጥረዋል።
የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ቀን 10 ሰዓት ላይ…
ሀዲያ ሆሳዕና ምድረ ገነት ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ምድረ ገነት ሽረን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕናን ግቦች ብሩክ በየነ በፍጹም ቅጣት ምት፣ ኤልያስ አህመድ እና ሱራፌል ተመስገን ሲያስቆጥሩ፤ ተካልኝ ደጀኔ የምድረ ገነት ሽረን…
ነገሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ እና ወላይታ ድቻ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የነገሌ አርሲን ግብ ገ/መስቀል ዱባለ ሲያስቆጥር÷ የወላይታ ድቻን ካርሎስ ዳምጠው በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።…
በኦሬዶ ዶሃ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሬዶ ዶሃ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
በዚህም በወንዶች ማራቶን አትሌት ታምራት ቶላ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ37 ሰኮንድ በመግባት የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸንፏል።
በውድድሩ ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች አሰፋ ቦኪ እና ቦኪ ድሪባ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ…
ሴኔጋል ግብጽን በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሴኔጋል ግብጽን በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፋለች።
ምሽት 2 ሰዓት ላይ በተጀመረው ጨዋታ ሴኔጋል ግብጽን 1 ለ 0 ስትረታ ሳዲዮ ማኔ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ለፍጻሜ ያለፈችው ሴኔጋል ከሞሮኮ እና ናይጀሪያ አሸናፊ…
የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ይካሄዳሉ።
ዛሬ ምሽት 2፡00 ሰዓት ላይ በሚደረገው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚዎቹ ሴኔጋል እና ግብጽ ይገናኛሉ።
በዚህ ጨዋታ ላይ የቀድሞ የቡድን አጋር የነበሩት የሴኔጋሉ ሳዲዮ ማኔ…