Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የቡድኑን ዋና እና ረዳት አሰልጣኞቹን አገደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ በዋና አሰልጣኝ፣ ረዳት አሰልጣኞች እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ላይ ጊዜያዊ እገዳ መጣሉን አስታወቀ። የስፖርት ማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ ባደረገው ስብሰባ የዋናውን እግር ኳስ ቡድን ወቅታዊ አቋም በሰፊው ከገመገመ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል። በዚህም በሶስቱ አሰልጣኞች ላይ ጊዜያዊ እገዳ በመጣል ዋናውን ቡድን በማሰልጠን ተግባር ላይ እንዳይሳተፉ ውሳኔ አሳልፏል። እንዲሁም የቴክኒክ ኮሚቴው እንዲሰናበት ሥራ አመራር ቦርዱ ወስኗል።…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ወልቂጤ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ አንድ ጨዋታ ተደርጓል። እንግዳው ወልቂጤ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ተጨውተው አዳማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ፕሪሚየር ሊጉ ነገም ሲቀጥል ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጭ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ይጫወታል። እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ባህር ዳር…

አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ሊያደርጉት የነበረው ተጠባቂ ጨዋታ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ። ጨዋታው የተራዘመው የግሪኩ እግር ኳስ ክለብ ኦሊምፒያኮስ ባለቤት ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ በትናንትናው ዕለት በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው።…

አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ 24 ተጫዋቾችን ጠሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ2021ዱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 24 ተጫዋቾችን ጠርቷል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዋልያዎቹ ከኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ ነው። ተጫዋቾቹ ከ13 የኘሪሚየር ሊጉ ክለቦች የተመረጡ ሲሆን፥ ለግብፁ አል መካስ እግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ…

4ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ ችቦ በመቐለ ተለኮሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ 4ኛው ዙር የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን ችቦ የመለኮስ ስነስርዓት በመቐለ ከተማ ተካሄደ፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን የቶኪዮ 2020 ብሄራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ የትግራይ…