Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡ በወንዶች በተደረገው ውድድር አትሌት ሃፍታሙ አባዲ 2 ሰዓት ከ 06 ደቂቃ ከ52 ሰኮንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቋል። በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ከማል ሁሴን ሦስተኛ  ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሷል፡፡ በሴቶች ደግሞ አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ46 ሰኮንድ በመግባት ነው ውድድሯን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው፡፡
Read More...

ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጀመሪያ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል አቤል ያለው በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ዳንላንድ ኢብራሂም የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጫዋች አቤል ያለው ላይ በሰራው ጥፋት…

አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ የግማሽ ማራቶን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል። አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን ለመጨረስ 1 ሰዓት 01 ሰኮንድ ከ21 ማይክሮ ሰኮንድ ፈጅቶበታል፡፡ በሴቶች ዘርፍ በተደረገ ውድድር ደግሞ አትሌት መስከረም ማሞ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በሌላ ዜና በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት…

በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት አይናለም ደስታ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ50ኛው በኔዘርላንድስ አምስተርዳም ማራቶን የሴቶች ውድድር አትሌት አይናለም ደስታ አሸንፋለች፡፡ በውድድሩ ብርቱካን ወልዴ 2ኛ ስትወጣ መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የአምስተርዳም ማራቶንን ማሸነፍ ችለዋል፡፡ የአምስተርዳም…

የአዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ተካሔደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 29ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡ መነሻውን  እና  መድረሻውን ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ባደረገው ውድድር በወንዶች አትሌት አበባው ደሳለኝ ከመቻል በቀዳሚነት በመግባት ውድድሩን ሲያሸንፍ፤ በግል የተወዳደሩት አትሌት አስራር ሀይረዲን እና ቶልቻ ተፈራ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን…

ሊቨርፑል ከማንቼስተር ዩናይትድ …

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ማንቼስተር ዩናይትድን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ የሊጉን ዋንጫ በተመሳሳይ 20 ጊዜ ማሳካት የቻሉትን ሁለቱን ቡድኖች በሚያገናኘው ጨዋታ÷ ወቅታዊ ብቃታቸው ተመጣጣኝ ባይሆን እንኳን በየትኛውም አጋጣሚ እርስ በርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ…

ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሊጉ 8ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የመጀመሪያ ጨዋታ ቼልሲ ኖቲንግሃም ፎረስትን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ነው ያሸነፈው። በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ምንም ግብ ማስቆጠር ያልቻሉት ቼልሲዎች በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ተጫዋቾችን በመቀየርና…