ስፓርት
አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቫሌንሺያ ሜዲዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረወሰንን በመስበር ጭምር አሸነፈ፡፡
አትሌቱ ርቀቱን ያጠናቀቀው 57 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት መሆኑን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡
የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በዑጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ተይዞ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
Read More...
የኮምቦልቻ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች የሰላም የእግር ጉዞ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች የሰላም የእግር የእግር ጉዞ አድርገዋል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሙሐመድ አሚን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ከተማዋ በሰላምና በልማት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡
ከልማት የሚገኘውን ጥቅም ዘላቂ ለማድረግም ማኅበረሰቡ ሰላሙን አስጠብቆ መቀጠል እንዳለበት…
አርሰናል ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዛሬው የጨዋታ መርሐ-ግብር መሠረት÷ ክሪስታል ፓላስ ከቶተንሃም ሆትስፐር፣ ቼልስ ከኒውካስል እንዲሁም ዌስትሃም ከማንቼስተር ዩናይትድ በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡
በሌላ በኩል ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ አርሰናል ከሊቨርፑል የሚያደርጉት…
ማንቸስተር ሲቲ የሊጉ መሪ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማንቸስተር ሲቲና ብሬንትፎርድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 11 ሰዓት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ማንቸስተር ሲቲ ሳውዝአምፕተንን 1ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ሲያሸንፍ ብሬንትፎርድ ደግሞ ኢፕስዊች ታውንን 4ለ3 ረትቷል፡፡
አስቶንቪላ ከቦርንሞውዝ 1ለ1 እንዲሁም ብራይተን…
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብሮች በዛሬው እለት ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡
ቀን 11 ሰዓት ላይ በሊጉ ሰንጠረዥ በ20 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ሳውዝአምፕተንን ያስተናግዳል።
በተመሳሳይ ሰዓት አስቶንቪላ ከቦርንሞውዝ፣ ብሬንትፎርድ ከኢፕስዊች ታውን፣ ብራይተን…
አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ተሰምቷል።
አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ውጣ ውረድን አልፎ በርካታ ድልን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት የተቀዳጀ ጠንካራ…
የአትሌት መዲና የ5 ሺህ ሜትር ውጤት በክብረ-ወሰንነት ፀደቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) - በኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የ5000 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር የተመዘገበው ውጤት በክብረ-ወሰንነት ፀደቀ፡፡
ባለፈው ወር በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ሩጫ የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና በ14 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ 89 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡
በአትሌት ጥሩነሽ…