Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ባሕር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ባሕር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡ የባሕር ዳር ከተማን ግቦችም ፍሬው ሰለሞን እና ፍጹም ዓለሙ አስቆጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ 1 ሠዓት ላይ በተካሄደው የዛሬ መርሐ-ግብር ዎላይታ ድቻ ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ካርሎስ ዳምጠው በ67ኛው ደቂቃ ኳሷን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ባሕር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ይገናኛሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት ባሕር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና 10 ሠዓት ላይ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከወዎላይታ ድቻ 1 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር አመላክቷል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ፡፡ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት አሰልጣኝ ቴን ሃግ ስኬታማ ጉዞ እያደረጉ አይደለም በሚል ትችት ሲሠነዘርባቸው ቆይቷል፡፡ ቀያይ ሰይጣኖቹ ትናንት ባደረጉት የፕሪሚየር ሊጉ ዘጠነኛ ሣምንት ጨዋታ በዌስት ሃም 2 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ በክለቡ…

4 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ታምራት ቶላ፣ ትዕግስት ከተማ እና ሱቱሜ አሰፋ የ2024 ከስታዲየም ውጭ የወንዶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ ላይ በዕጩነት ተካተቱ፡፡ አትሌቶቹ በውድድር ዓመቱ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ባስመዘገቡት ውጤት ነው ለዕጩነት መካተት የቻሉት። በውድድር ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ…

አርሰናል እና ሊቨርፑል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሣምንት ጨዋታ በሜዳው ሊቨርፑልን ያስተናገደው አርሰናል 2 አቻ ተለያይቷል። 1 ሠዓት ከ30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ፥ ቡካዮ ሳካ እና ሚኬል ሜሪኖ የመድፈኞቹን ግቦች አስቆጥረዋል። ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ሞሐመድ ሳላህ ደግሞ የሊቨርፑልን ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።…

ቼልሲ ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ዌስትሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ቼልሲ ከኒውካስል ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ግቦቹን ጃክሰን እና ፓልመር አስቆጥረዋል፡፡ የኒውካስልን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኢሳቅ አስቆጥሯል፡፡ ክሪስታልፓላስ ቶተንሃምን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ግቧን ማቴታ አስቆጥሯል፡፡…

በፍራንክፈርት ማራቶን አትሌት ሀዊ ፈይሳ ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ፍራንክፈርት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ውድድር  አትሌት ሀዊ ፈይሳ ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች። አትሌት ሀዊ ፈይሳ ውድድሩን  2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በመግባት ማሸነፏን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡