ስፓርት
በሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ ሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸነፉ።
በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው በሲድኒ ማራቶን አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ 2:21:40 በሆነ ሰዓት በመግባት የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ውድድሩን አሸንፋለች።
አትሌት ሩቲ አጋ 2:23:09 እንዲሁም አትሌት ጎይተቶም ገብረሥላሴ 2:24:16 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
በወንዶች ደግሞ ኬኒያዊው አትሌት ብሪሚን ሚሶይ 2:06:17 በሆነ…
Read More...
ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሲቀጥል ቶተንሃም አርሰናልን ያስተናግዳል
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በሰሜን ለንደን ደርቢ ቶተንሃም ሆትስፐር አርሰናልን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
12 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ዎልቭስ ኒውካስል ዩናይትድን ያስተናግዳል።
ትናንት በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር…
በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ሲቲ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግዷል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስቴዲየም ብሬንትፎርድን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የማንቺስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኧርሊግ ሃላንድ ሲያስቆጥር የንቦቹን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዮዋኔ ዊሳ አስቆጥሯል፡፡
ኧርሊንግ…
ማንቼስተር ዩናይትድ ሳውዝሃምፕተንን 3 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ሴንት ሜሪ አቅንቶ ሳውዝሃምፕተንን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ማቲያስ ዴሊት፣ ማረከስ ራሽፎረድ እና አሊሃንድሮ ጋርናቾ አስቆጥረዋል፡፡
8፡30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ በሳዝውሃምፕተን በኩል ጃክ ስቴፈንስ በ79…
ፕሪሚየር ሊጉ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ ይመለሳል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ በሚደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ይመለሳል፡፡
በዚሁ መሠረት በአራተኛ ሣምንት መክፈቻ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሳውዝሃምፕተን 8 ሠዓት ከ30 ላይ በሴንት ሜሪ ስታዲየም ይገናኛሉ፡፡
እንዲሁም 11 ሠዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ፣ ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም…
በ5 ሺህ ወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው ገቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም ብራሰልስ በተካሄደ የ2024 ዳያመንድ ሊግ 5 ሺህ ወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገቡ።
በውድድሩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 12:43.66 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ቀዳሚ ሆኗል።
አትሌት በሪሁ አረጋዊን በመከተል ሀጎስ ገብረህይወት 12:44.25…
የክሪስቲያኖ ሮናልዶ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቁጥር 1 ቢሊየን ደረሰ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእግር ኳስ ኮከቡ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቁጥር 1 በሊየን መድረሱ ተገለፀ፡፡
ሮናልዶ 1 ቢሊዮን ተከታይ ያገኘው በሚጠቀማቸው የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሆን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ ተከታይ ያለው የመጀመሪያው ግለሰብ ለመሆን በቅቷል።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ተከታዮቹን ያገኘው…