ስፓርት
በማራቶን ሪሌይ ውድድር የኦሮሚያ ፖሊስ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሠመራ ከተማ በተካሔደው 18ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌይ ውድድር ኦሮሚያ ፖሊስ አሸንፏል፡፡
በክለቦች መካከል በተካሔደው የማራቶን ሪሌይ ውድድር÷ የኦሮሚያ ፖሊስ አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያና የገንዘብ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በዚሁ የውድድር መርሐ ግብር ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ገንዘብና ሜዳሊያ ተሸልሟል፡፡
ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብና የነሐስ ሜዳሊያ መሸለሙን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡…
Read More...
ካሪም ቤንዜማ ከዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው አጥቂ ካሪም ቤንዜማ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከዓለም ዋንጫ ጨዋታ ውጪ መሆኑን ብሔራዊ ቡድኑ አስታውቋል፡፡
ካሪም ቤንዜማ ከውድድሩ ውጭ የሆነው በትናንትናው ዕለት በልምምድ ላይ ሳለ ባጋጠመው የጡንቻ ጉዳት መሆኑን የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡
የ2022 የባሎንዶር አሸናፊው…
የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በወንዶች አትሌት አቤ ጋሻው ለሦስተኛ ጊዜ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በወንዶች ከአማራ ማረሚያ ቤት አትሌት አቤ ጋሻው አሸንፏል፡፡
አትሌት አቤ ጋሻው የዘንድሮውን ሲያሸንፍ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግሯል፡፡
አትሌት ኃይለማርያም አማረ ከፌደራል ማረሚያ ሁለተኛ እና አትሌት ገመቹ ዲዳ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ…
የዓለም ዋንጫ ዛሬ ይጀምራል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቀው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ በኳታር ይጀመራል።
የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ 60 ሺህ ገደማ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ባለው አል በይት ስታዲየም ይካሔዳል፡፡
በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ የውድድሩ ሳውንድ ትራክ ተብሎ በፊፋ እውቅና የተሰጠው "ሃያ ሃያ" (አብሮነት ይሻላል) የሚለው ሙዚቃ…
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሔደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂ አትሌቶችን ጨምሮ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በሩጫው የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ÷ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ፣ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናኒሴ ጫሊ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ…
በፕሪሚየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በ8ኛ ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
በዚህም 10 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡…
በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሄደዋል።
10 ሰአት ላይ በተደረገ የመጀመሪያው ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ፉአድ ፈረጃ፣ ፍፁም ጥላሁን እና ያሬድ ባየህ የባሕርዳርን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የኢትዮጵያ ቡና ጎል ሮቤል ተክለሚካኤል አስቆጥሯል፡፡
ባሕርዳር ከተማ…