Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ በአቦት ወርልድ ማራቶን ደረጃ በሴቶች ቀዳሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ በአቦት ወርልድ ማራቶን ሜጀርስ የደረጃ አወጣጥ መሰረት በሴቶች ቀዳሚ ሆናለች፡፡ ደረጃው የወጣው በ6 ዋና ዋና የማራቶን ውድድር ማለትም በበርሊን፣ በለንደን፣ በቦስተን፣ በቶኪዮ፣ በቺካጎ እና በኒውዮርክ የማራቶን ውድድር ውጤት መሰረት ሲሆን አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ የውድድር አመቱ ምርጥ አትሌት ሆናለች፡፡ የውድድር ዘመኑን በበላይነት ማጠናቀቋን ተከትሎ አትሌቷ የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆኗንም ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡…
Read More...

በፕሪሚየር  ሊጉ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ዛሬ ቀን 10 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን በይገዙ ቦጋለ ሁለት ግቦች  2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በባህርዳር ደካማ ጊዜን ያሳለፈው ሲዳማ ቡና ስዩም ከበደን የቡድኑ አሰልጣኝ ካደረገ ወዲህ ሁለት…

በጥሎ ማለፉ ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ እንዲሁም ባየር ሙኒክ ከፒ ኤስ ጂ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዕጣ ድልድል ይፋ ሆኗል። ከየምድባቸው 1ኛ እና 2ኛ ሆነው ያጠናቀቁ ቡድኖችን በሚያገናኘው ጥሎ ማለፍ 16 ቡድኖች ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል የደርሶ መልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአምናውን የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ ከሊቨርፑል እንዲሁም የጀርመኑን ሃያል ክለብ ባየር ሙኒክ…

በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በአሜሪካ በተካሄደው የኒውዮርክ ማራቶን በወንዶች አትሌት ሹራ ቂጣታ 2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት አሻነፊ ሰሆን፥ በሴቶች አትሌት ጎቲቶም ገብረስላሴ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን…

በሶዌቶ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ አፍሪካ ሶዌቶ በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ርቀቱን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡ በወንዶች ማራቶን ዳባ ኤፋ 42 ኪሎ ሜትሩን 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ በመግባት ቀዳሚ ሲሆን ፥ የሀገሩ ልጅ ጋዲሳ በቀለ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ በሴቶች…

ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድደር ኢትዮጵያ ዩጋንዳን አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድደር ኢትዮጵያ ዩጋንዳን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ የኢትዮጵያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ከድር ዓሊ ጨዋታው በተጀመረ 60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ምድቧን በ4 ነጥብ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፏን…

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ድሬዳዋ ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ 10 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና መቻል ባደረጉት ጨዋታ ወላይታ ድቻ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግብ ቃልኪዳን ዘላለም በ31ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገ…