Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር እና ድሬዳዋ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ድሬዳዋ ላይ በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል። 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከባሕር ዳር ባደረጉት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ባለ ድል ሆኗል። በጨዋታው ባሕርዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ2 አሸንፏል፡፡ የማሸነፊያ ጎሎችን ተስፋዬ ታምራት፣ ፉዐድ ፈረጃ እና ሀብታሙ ታደሠ አስቆጥረዋል፡፡ የኢትዮጵያ መድንን ጎል ደግሞ ብሩክ ሙሉጌታ እና ኪቲካ ጅማ በጭማሪ ሰዓት አስቆጥረዋል፡፡ ምሽት 1 ሰአት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ…
Read More...

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በድሬዳዋ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጀመራል። በቀጣዮቹ 5 ሳምንታት በድሬዳዋ የሚካሄዱት ጨዋታዎች የሰዓት ማሻሻያ የተደረገባቸው ሲሆን÷ጨዋታዎቹ 10 ሰዓት እና ምሽት 1 ሰዓት የሚካሄዱ ይሆናል። በመርሐ ግብሩ መሰረትም ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ…

ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ሁለት አቻ ተለያዩ፡፡ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡

ሊግ ኩባንያው በ5ኛ ሳምንት በተስተዋሉ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ በ5ኛ ሳምንት በተስተዋሉ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡ የኩባንያው ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ባደረገው ስብሰባ በ5ኛ ሳምንት በተደረጉ ውድድሮች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የሥነ ምግባር ሪፖርት በመመርመር የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በተጫዋቾች…

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የባህር ዳር ቆይታን የሚቋጨው ተጠባቂ ጨዋታ ዛሬ 10 ሰዓት ተካሂዷል፡፡ በጨዋታው ፋሲል ከነማና ባህርዳር ከተማ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የከፍተኛ ሊግ ውድድር ህዳር 17 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ሊግ ውድድር ህዳር 17 ቀን 2015ዓ.ም  እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ የከፍተኛ ሊግ ውድድሩ ህዳር 3 ቀን 2015ዓ.ም እንደሚጀምር  መገለፁ  ይታወሳል፡፡ ሆኖም  ውድድሩ   በተጠቀሰው  ቀን እንዲጀመር መወሰኑ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የዝግጅት ጊዜ እንደሚያጥራቸው የክለብ…

በፕሪሚየር ሊጉ ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 5ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ 7 ሰዓት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡ በጨዋታው ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የማሸነፊያ ግቡን በ68ኛ ደቂቃ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን…