ስፓርት
ሜክሲኮ እና ፖላንድ በአቻ ውጤት ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የዓለም ዋንጫ ምሽት ላይ በተካሄደ ጨዋታ የተገናኙት ሜክሲኮ እና ፖላንድ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ፖላንድ ያገኘችውን የፍጹም ቅጣት ምት ወደ ውጤት መቀየር ሳትችል ቀርታለች፡፡
የ2022 የዓለም ዋንጫ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 4 ሰዓት ላይ ፈረንሳይ ከአውስትራሊያ ይጫወታሉ፡፡
ቀደም ሲል በተካሔዱ ሁለት ጨዋታዎች ሳዑዲ ዓረቢያ አርጀንቲናን 2 ለ1 ስታሸንፍ÷ ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወቃል፡፡ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ…
Read More...
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስምምነት ከማንቼስተር ዩናይትድ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከክለቡ ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት ከማንቼስተር ዩናይትድ መልቀቁ ይፋ ሆኗል፡፡
ሮናልዶ በኦልትራፎርድ ቆይታው በ346 ጨዋታዎች 145 ጎሎችን በማስቆጠር ላበረከተው አስተዋፅዖ ያመሰገነው ክለቡ÷ በቀጣይ የእግር ኳስ ሕይወቱ የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ…
ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምድብ አራት የተደለደሉት ዴንማርክ እና ቱኒዚያ ያረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቋል፡፡
10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደረጉት ዴንማርክ እና ቱኒዚያ አቻ በሆነ ውጤት መለያየታቸውን ተከትሎ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡
በዚህም የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከተጀመረ ጀምሮ ያለምንም ጎል የተጠናቀቀ የመጀመሪያው ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡…
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ሲዳማ ቡና መቻልን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ÷ ጎሎቹን ፍሬው ሰለሞን በ17ኛው እና ሙሉዓለም መስፍን በ75ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዋሳ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ጎሎቹንም÷…
አርጀንቲና ባልተጠበቀችው ሳዑዲ የዓለም ዋንጫውን በሽንፈት ጀምራዋለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ሶስተኛ ቀን ውሎ ሳዑዲ ዓረቢያ ያልተጠበቀ ድል አስመዝግባለች።
ከደቡብ አሜሪካዋ አርጀንቲና ጋር የተጫወተችው ሳዑዲ ከመመራት ተነስታ 2 ለ 1 አሸንፋለች።
በጨዋታው ሊዮኔል መሲ በ10ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠረው ጎል አርጀንቲና 1 ለ 0 መምራት ብትችልም ሳዑዲዎች በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታውን…
በሦስተኛው ቀን የዓለም ዋንጫ ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሦስተኛ ቀኑን በያዘው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ፡፡
በምድብ ሦስት የተደለደለችው አርጀንቲና ቀን 7 ሰአት ላይ ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ትጫወታለች፡፡
ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው በሆነው የዓለም ዋንጫ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር በድል ለመመለስ ዛሬ አንድ ብሎ ይጀምራል።
በዚሁ ምድብ የደለደሉት ሜክሲኮ እና…
በአለም ዋንጫ ሴኔጋል በኔዘርላንድስ ተሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው ቀን የኳታር የዓለም ዋንጫ ጨዋታ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 ተሸንፋለች፡፡
የኔዘርላንድስን የማሸነፊያ ጎሎች የፒኤስቪው አጥቂ ኮዲ ባክፖ እና የአያክሱ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ዴቪ ኬላሰን አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው የተሳኩ ሙከራዎችን ማድረግ የቻለችው ሴኔጋል ኔዘርላንድስን መፈተን ብትችልም…