Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ጋምቢያ በእግር ኳስ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር ጋምቢያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡ ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ጋምቢያ ከጊኒ ጋር ባደረገችዉ ጨዋታ በሙሳ ባሮ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 በማሸነፍ ነው በእግር ኳስ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ሩብ ፍፃሜ መቀላቀል የቻለችዉ፡፡ በሌላ ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገሯ ካሜሩን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በርካታ ተጫዋቾቿን ያጣችውን ኮሞሮስ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው አልፋለች።…
Read More...

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻዉ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ጥር 15፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻዉ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ዛንዚባር ላይ በተደረገው ይህ ጨዋታ የታንዛኒያን የማሸነፊያ ጎል ክሪሲያ ጆንባራ በ64ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥራለች፡፡ መረጃዉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው ፡፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ…

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው 11ኛው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ራስ ሐይሉ ጅምናዚየም ዛሬ ተጀምሯል። በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች…

በሀገሪቱ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን የስፖርቱ ዘርፍ የላቀ ድርሻ አለው- አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ስፖርት ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የስፖርት ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ርስቱ ይርዳ ፥ ስፖርት ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ስብዕና ለመገንባት ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ወጣቶች ያላቸውን ዝንባሌ በመጠቀም…

21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ • በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው፣በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ አሸናፊ ሆነዋል።

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 25 ሺህ ሯጮች የሚሳተፉበት 21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመዲናችን በደማቅ ሁኔታተካሄደ። የ21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ከጎረቤት አገሮች የመጡ አትሌቶች እና የሩጫው ተሳታፊዎች ተገኝተዋዋል።…

ኢትዮጵያ በታላቁ ሩጫ ላይ ናት! እንኳን ለ21ኛው የታላቁ ሩጫ ዝግጅት አደረሳችሁ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 21ኛውን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዝግጅት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን፣ ግጭትንና ጦርነትን፣ መለያየትንና መከፋፈልን ከኋላዋ ጥላ፤ ብልጽግናንና ሥልጣኔን፣ ሰላምንና መቻቻልን፣ አንድነትንና መግባባትን ለማስፈን ወደፊት እየሮጠች ነው…

ኅብረተሰቡ ለገቢ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀው የእግር ኳስ ጨዋታ እየተዝናና ወገኑን እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረተሰቡ በኢትዮጵያ ዳያስፖራና የአገር ቤት ቡድን የቀድሞ ታዋቂ ተጫዋቾች መካከል በሚካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ኳስ ጨዋታ እየተዝናና ወገኖቹን እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ። የኢትዮጵያ ዳያስፖራና የአገር ቤት ቡድን የእግር ኳስ ጨዋታው በመጪው እሁድ ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድ የዝግጅቱ…