Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በ15ኛው ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ15ኛው ሣምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል፡፡ ዛሬ ቀን 9 ሰዓት ላይ በጀመረው ጨዋታ የፋሲል ከተማን ሁለት የአሸናፊነት ጎሎች ሽመክት ጉግሳ አስቆጥሯል፡፡ ኦኪኪ ኦፎላቢ እና በረከት ደስታ ቀሪዎቹን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ በላፉት 4 ጨዋታዎች ደካማ አቋም ያሳየው ፋሲል ከነማ÷ ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ ከሀዋሳ ከተማ ጋር በእኩል 26 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡…
Read More...

አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው በስፔን በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው በስፔን ላ ፕላና በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበች፡፡ አትሌቷ 29:14 በሆነ ሰዓት በመግባት ነው አዲስ ክብረ ወሰን ያስመዘገበችው፡፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ…

የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን የመሩት ረዳት ዳኛ ከውድድሩ ተሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን የመሩት ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ ከውድድሩ መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡ በተጠናቀቀው የ13ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ ላይ ረዳት ዳኛው ባሳዩት የዳኝነት ስህተት ነው ቅጣቱ የተላለፈባቸው፡፡ በዕለቱ ወልቂጤ ከተማ በመጀመሪያው…

በቱራን የዓለም የቤት ውስጥ ቱር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት ምሽት በፖላንድ በተደረገ ቱራን የዓለም የቤት ውስጥ ቱር ውድድር በሁለቱም ጾታዎች በተለያዩ መርሃ ግብሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በዚሁ መሠረት በወንዶች 3000 ሜትር አትሌት ለሜቻ ግርማ 7:31.09 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር ሰለሞን…

በሣምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የአገር አቋራጭ እና የጎዳና ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሣምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ እና እሁድ በተካሄዱ አገር አቋራጭ እና ዓለም አቀፍ የጎዳና ውድድሮች እንዲሁም በስፔን ሲቪላ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በዚሁ መሠረት በወንዶች አስራር ሃይረዲን 2፡04፡43 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡…

በራስ አል ካምሃ ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትላንት በተካሄደው የራስ አል ካምሃ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ግርማዊት ገ/እግዚአብሄር አሸንፋለች። አትሌት ግርማዊት ገ/እግዚአብሄር 1:04:14 በሆነ ሰዓት በመግባት ነው የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድርን ያሸነፈችው፡፡ በዚሁ ውድድር አትሌት ቦሰና ሙላቴ 1:05.46 በሆነ ሰዓት በመግባት 5ኛ ደረጃን…

በፓን አፍሪካ ትምህርት ቤቶች ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎች አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓን አፍሪካ ትምህርት ቤቶች ውድድርን ኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎች አሸንፋለች፡፡ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አስተናጋጅነት ዛሬ የተጀመረው የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች ውድድር በተለያዩ ጨዋታዎች በሁለቱም ፆታዎች ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ ድል ማስመዝገቧ ተገልጿል። በወንዶች አስተናጋጇ…