ስፓርት
ካርሎ አንቸሎቲ የኤቨርተን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።
ኤቨርተን ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲን በ4 ዓመት ከግማሽ ኮንትራት ነው የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ የቀጠረው።
በያዝነው የፈረንጆቹ ወር የመጀመሪያ ላይ ከናፖሊ የተሰናበቱት አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ከሁለት ሳምንት በፊት ከጉዲሰን ፓርክ የተሰናበቱትን አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫን ተክተው ነው ክለቡን የሚረከቡት።
ሶስት ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያነሱት…
Read More...
አርቴታ አርሰናልን በአሰልጣኝነት ተረከበ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ አርሰናል ሚካኤል አርቴታን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።
ክለቡ የቀድሞ አማካዩን በዋና አሰልጣኝነት ለመቅጠር ለማንቼስተር ሲቲ በሚሰጠው የካሳ ክፍያ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሱም ነው የተነገረው።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬን ካሰናበተ በኋላ የክለቡን የቀድሞ…
የኢትዮጵያ ከ20 እና 17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ከ20 እና 17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችን ይፋ አድርጓል።
የአሰልጣኞቹ ምርጫ እና ምደባ በእግር ኳስ ልማት ምክትል ፅህፈት ቤት ኃላፊ፣ በሴቶች እግር ኳስ ልማት፣ በውድድር ቋሚ ኮሚቴ እና የቴክኒክ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ነው የተካሄደው።…
አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የሴካፋ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ሆነው መመረጣቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
የመካከለኛውና ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ማህበር/ሴካፋ/ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የአባል ሀገራቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶች በተገኙበት በኡጋንዳ…
የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ የእርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ የ3000 ሜትር መሰናክል፣ የእርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር እየተካሄደ ነው።
አትሌቲክስ ውድድሩ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ መጀመሩን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
በዛሬው እለትም የአሎሎ ውርወራ ማጣሪያና ፍፃሜ፣ የስሉስ…
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 6፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም በነገው ዕለት ይጀመራል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአጭር፣ በመካከለኛ ርቀት፣ በ3 ሺህ ሜ.መሰናክል፣ በእርምጃና በሜዳ ተግባራት ከታህሳስ 7 እስከ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበበ ስታዲየም ነው የሚካሄደው፡፡
በመክፈቻው እለትም የአሎሎ ውርወራ…
በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፍነው ቅዳሜና እሁድ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በቻይና በተካሄደ የሼንዚን የወንዶች ማራቶን ውድድር ታደሰ ቶላ እና ተረፈ ደበላ ተክታትለው በመግባት ከአንድ እስከ ሁለተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ በቀለ ሙሉነህ ሰባተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።…