ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሰበታ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሰበታ ከተማን 3 ለ 2 አሸነፈ፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና አቡበክር ናስር ሁለት እንዲሁም ሃብታሙ ታደሰ አንደኛውን ጎል አስቆጥረዋል፡፡
የሰበታ ከተማን ጎሎች ደግሞ እስራኤል እሸቱ እና ቃል ኪዳን ዘላለም ማስቆጠር ችለዋል፡፡
የሊጉ አምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ከሰዓት የሚቀጥል ሲሆን÷ ጅማ አባ ጅፋር ከሃዋሳ ከተማ ጋር እንደሚጫወቱ የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል።…
Read More...
ትናንት በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ትናንት ምሽት በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች በተካሄዱ ውድድሮች ድል ቀንቷቸዋል።
በዚህም በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ያለምዘርፍ የኋላው በ31 ደቂቃ 17 ሰከንድ፣ በባርሴሎና በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ደግሞ ገንዘቤ ዲባባ ርቀቱን በ15 ደቂቃ በማጠናቀቅ አሸናፊ…
ለሃገር ባለውለታ አንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ መቶ አንጋፋ አትሌቶች ስጦታ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም አበረከተላቸው።
ለእያንዳንዳቸው አንጋፋ አትሌቶች የሶስት ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታውን የአንጋፋ አትሌቶች ፕሬዚዳንት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ አማካኝነት ተበርክቷል፡፡
ስጦታው በየተወሰነ ጊዜ ቀጣይነት…
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በባርሴሎና የዓለም ክብረወሰንን ለማሻሻል ትሮጣለች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በባርሴሎና የዓለም ክብረወሰንን ለማሻሻል ትሮጣለች።
የዓለም 1 ሺህ 500 ሜትር ክብረወሰን ባለቤቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ነገ በባርሴሎና በሚካሄደው የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረወሰንን ለማሻሻል እንደምትሮጥ ታውቋል።
ገንዘቤ በ5 ሺህ ሜትር የሲፈን ሀሰንን 14 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ ፥…
በፕሪሚየር ሊጉ ወልቂጤ ከተማ ባህርዳር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸነፈ፡፡
በጨዋታው ቶማስ ስምረቱ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤…
በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ወላይታ ዲቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማ ወላይታ ዲቻን 3 ለ 2 አሸነፈ፡፡
በጨዋታው ሙጂብ ቃሲም ለፋሲል ከነማ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ሐት ትሪክ ሰርቷል፡፡
የወላይታ ዲቻን ጎሎች ደግሞ ስንታየሁ መንግስቱ እና ፀጋዬ…
በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ0 አሸንፏል፡፡
የድሬዳዋ ከተማን ግብ አስቻለው ግርማ እና ጄኒያስ ናንጄቦ አስቆጥረዋል፡፡
የሊጉ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ከሰዓትም የሚቀጥል ሲሆን ፋሲል ከነማ ከወላይታ ዲቻ…