ስፓርት
የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ አስተናጋጇ ካሜሮን ገለፀች።
ትናንት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) እና የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ የካፍ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ዋንጫ ከፈረንጆፐቹ ጥር 1 እስከ 29 ድረስ እንደሚካሄድ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ይዘጋጅ የነበረው በወርሃ ሰኔ እና ሐምሌ ላይ የነበረ ቢሆንም፥ እነዚህ ወራት በካሜሩን ዝናባማ ስለሚሆኑ ወደ ጥር እንዲዘዋወር ተደርጓል ተብሏል።
የጊዜ ለውጡ የተደረገው…
Read More...
ወላይታ ድቻ የቀድሞ አሰልጣኙ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ጥር 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ።
ክለቡ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በ8ኛ ሳምንት በሜዳቸው ላይ መሸነፋቸውን ተከትሎ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙበትን ማስረጃ በመያዝ ወደ ምድብ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡን አስታውቋል።
ክለቡ በቀጣይ ከጅማ አባጅፋር…
ባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በማሰናበት ኪኬ ሴቲዬን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስፔኑ ሀያል የእግር ኳስ ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በማሰናበት ኪኬ ሴቲዬን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ተሰምቷል።
የ55 ዓመቱ አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ባርሴሎናን በመሩበት ጊዜ ክለቡ ሁለት የስፔን ላሊጋ ዋንጫዎችን እንዲያነሳ እና የዘንድሮውን የላሊጋ ውድድር በግብ ልዩነት እንዲመራ አድርገዋል።…
በኔዘርላንድስ ግማሽ ማራቶን አትሌት ፀሃይ ገመቹ አሸናፊ ሆናለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኔዘርላንድስ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር አትሌት ፀሃይ ገመቹ አሸናፊ ሆናለች።
አትሌት ፀሃይ ርቀቱን 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ስታሸንፍ፥ አትሌት ታደለች በቀለ ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች።
በተመሳሳይ በስፔኑ ሁዋን ሙጉዬርዛ አመታዊ የግማሽ ማራቶ ውድድር አትሌት ታደሰ ወርቁ…
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 03፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተካሂደዋል።
በዚህም ወልቂጤ ከተማን ከሜዳው ውጭ የገጠመው የአምናው ሻምፕዮን መቀሌ 70 እንደርታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ተረክቧል
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳው ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 2ለ1 በሆነ ውጤት…
የሀላባን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የሩጫ ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀላባን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የ8 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተካሄደ።
“ሴራችን ለሰላማችን” በሚል ሀሳብ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ውድድሩን ያስጀመረችው አትሌት ፋንቱ ምጌሶ “ሰላም ለሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ የሀላባ ብሄር የዘመን መለወጫ…
በቶኪዮ ኦሊምፒክ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ማስተላለፍ እንደማይቻል ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ የእጅ ምልክትን ጨምሮ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ማስተላለፍ እንደማይቻል ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቀጣዩ ሃምሌ ወር በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው ኦሊምፒክ ውድድር ላይ ለተወዳዳሪ አትሌቶች በተከለከሉ የደስታ አገላለጾች እና የሚያስተላልፏቸውን መልዕክቶች…