ስፓርት
ዋይኒ ሩኒ ከፕሌይ ማውዝ ጋር ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ዋይኒ ሩኒ ከእንግሊዝ ሻምፒየን ሽፑ ቡድን ፕሌይ ማውዝ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል፡፡
የ39 ዓመቱ የማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞ ኮከብ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሩኒ÷ በተደረጉ 23 የቻምፒየን ሽፕ ጨዋታዎች 4 ጊዜ ሲያሸንፍ በ13ቱ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
በአሰልጣኝነት ዘመኑ ስኬት የራቀው ዋይኒ ሩኒ የፕሌይ ማውዝ አሰልጣኝ ከመሆኑ በፊት÷ ከበርሚንግሃም ሲቲ በውጤት ቀውስ መሰናበቱ ይታወሳል፡፡
በተመሳሳይ የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ክለብ በሆነው ዲ ሲ ዩናይትድን…
Read More...
ኢትዮጵያ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ማጣሪያ ኢትዮጵያ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች፡፡
በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ማጣሪያ አንደኛ ዙር ኢትዮጵያ እና ዚምባብዌ ጨዋታቸውን ለማድረግ መርሐ ግብር እንደወጣላቸው ይታወሳል።
ሆኖም ዚምባብዌ ከውድድሩ ራሷን ማግለሏን በማሳወቋ የደርሶ መልስ ጨዋታዎቹ…
ኤ ሲ ሚላን ፓውሎ ፎኔስካን ከኃላፊነት አነሳ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን ሴሪ ኤው ክለብ ኤ ሲ ሚላን አሰልጣኝ ፓውሎ ፎኔስካን ከኃላፊነት ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል፡፡
ክለቡ አሰልጣኙን ያሰናበተው ኤ ሲ ሚላን በትናንትናው ዕለት ከሮማ ጋር አንድ አቻ ከተለያየ በኋላ ነው፡፡
በሴሪ ኤው እንዲሁም በአውሮፓ መድረክ ቡድኑ እያስመዘገበ ያለው ደካማ እንቅስቃሴ ለስንብቱ ምክንያት መሆኑም…
አሠልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጥሪው የቀረበው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አንደኛ ዙር ከዚምባብዌ ጋር በጥር ወር መጀመሪያ ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅት ነው፡፡
በዚሁ መሠረት ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች…
ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚያደርጉት ግጥሚያ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ ኦልድትራፎርድ ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል፡፡
ጨዋታው ምሽት 5 ሠዓት ላይ ሲደረግ በተደጋጋሚ ሽንፈት ጫና ውስጥ የሚገኘው የሩበን አሞሪም ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡…
ማንቼስተር ሲቲ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለወራት በውጤት ቀውስ ውስጥ የቆየው ማንቼስተር ሲቲ ከ4 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡
በገና በዓል ሰሞን ከሜዳቸው ውጭ ሌስተር ሲቲን የገጠሙት ሲቲዝኖቹ በሳቪኒሆ ሞሬራ እና ኤርሊንግ ሃላንድ ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡
በጨዋታው የመጀመሪያ ጎል ያስቆረው ብራዚላዊው…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 6 ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ሥድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በዚህም መሠረት 11 ከ30 ላይ ሌስተር ሲቲ በሜዳው የአምናውን ሻምፒየን ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡
እንዲሁም በተመሳሳይ ምሽት 12 ሠዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ ከሳውዝ ሃምፕተን፣ ኤቨርተን ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ፉልሃም ከበርንማውዝ…