Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የአትሌት መዲና የ5 ሺህ ሜትር ውጤት በክብረ-ወሰንነት ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) - በኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የ5000 ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር የተመዘገበው ውጤት በክብረ-ወሰንነት ፀደቀ፡፡ ባለፈው ወር በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ሩጫ የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና በ14 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ 89 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡ በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከ20 ዓመት በፊት የተመዘገበው 14 ደቂቃ 30 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ የውድድሩ ክብረ-ወሰን ነበር፡፡
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ  መቐለ 70 እንደርታ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ 5ተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በድሬዳዋ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ እናከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ የመቐለ 70 እንደርታ የማሸነፊያ ሁለት ጎሎችን ያሬድ ብርሃኑ ሲያስቆጥር አሸናፊ ሐፍቱ…

አቡበከር ናስር ሱፐር ስፖርት ዩናትድን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሲጫዎት የነበረው አቡበከር ናስር ሌላኛውን የደቡብ አፍሪካ ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን ተቀላቅሏል፡፡ የፊት መስመር አጥቂው በማሜሎዲ ሰንዳውንስ ቆታው ባጋጠመው ከበድ ያለ ጉዳት ምክንያት በክለቡ ያልተሳካ ገዜ መሳላፉ የሚታወስ ነው፡፡ አቡበከር በሰንዳውንስ አለመፈለጉን ተከትሎ ሱፐር ስፖርት…

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ አቅም አላት – የካፍ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ አቅም እንዳላት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞው የቦትስዋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ማክሊን ኮርቴዝ ሌትሺዊቲ ገለጹ። 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ትናንት…

የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ ጋር ጥቅምት 21 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚያደርገው የቻን ማጣሪያ ደርሶ መልስ ጨዋታ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ቀረበ፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት÷ በግብ ጠባቂ ዘርፍ ሰኢድ ሀብታሙ፣ በረከት አማረ እና ዳግም ተፈራ ተካትተዋል፡፡ አስራት ቱንጆ፣…

በኢትዮጵያ የወጣቶች ማዕከላት ዓላማቸውን እንዲያሳኩ የፊፋ ድጋፍ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በተሟላ መልኩ አገልግሎት መስጠትና የተቋቋሙበትን ዓላማ እንዲያሳኩ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ)…

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨዋታ በጁባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታዋን በደቡብ ሱዳን ጁባ እንደምታደርግ ተገለጸ፡፡ በዚሁ መሠረት የሀገራቱ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ጥቅምት 21 ቀን 2017 እና ጥቅምት 24 ቀን 2017 እንደሚከናወኑ መገለጹን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡