Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ደሳለኝ ዳኘው እና የግሌ እሸቱ በ2017 የጅማ ታላቁ ሩጫ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ደሳለኝ ዳኘው እና አትሌት የግሌ እሸቱ በ2017 የጅማ ታላቁ ሩጫ ውድድር አሸነፉ። ዛሬ ማለዳ በጅማ ከተማ በተደረገ የወንዶች 15 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ደሳለኝ ዳኘው በአንደኛነት ሲያጠናቅቅ፤ ጃፋር ጀማል ሁለተኛ እንዲሁም አብዮት ሞገስ ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን ጨርሰዋል፡፡ በተመሳሳይ በሴቶች በተደረገ የ15 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት የግሌ እሸቱ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፤ ሃና ዓለማየሁ እና አና ላውልሄር ተከታትለው በመግባት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።…
Read More...

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የማንቹሪያን ደርቢ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ የከተማ ተቀናቃኙን ማንቼስተር ሲቲን ምሽት 12 ሰዓት ከ 30 ላይ ያስተናግዳል። በውድድር ዓመቱ ወጥ ብቃት ማሳየት የተሳነው እና በ37 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።…

አትሌት ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃማይካ እየተካሄደ በሚገኘው ግራንድ ስላም ትራክ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አሸንፋለች። አትሌት ድርቤ ርቀቱን 4:04.51 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች። አትሌቷ በ800 ሜትር 2ኛ የወጣችበት ውጤት ተደምሮ በአጠቃላይ ያገኘችውን ነጥብ 20 ማድረሷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ…

ባለ ንስር ዐይኑ ጎል ቀማሚ – ኬ ዲ ቢ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቁጥሮች አይዋሹም ይባላል፤ በዘጠኝ ዓመት የውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት ቆይታው ከሪያን ጊግስ ቀጥሎ በፕሪሚየር ሊጉ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ስሙን በስኬት መዝገብ አስፍሯል። ጎል ከማይነጥፍበት የማንቸስተር ሲቲ የፊት መስመር ጀርባ በንስር ዐይኑ አሻግሮ በማማተር ኳስን ሲጠበብባት ዓለም የተመለከተው ኮከብ ከቁጥሮችም…

ኬቨን ዲብሮይን በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቤልጂየማዊው የማንቼስተር ሲቲ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዲብሮይን ከዘጠኝ ዓመት ቆይታ በኋላ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከቡድኑ ጋር እንደሚለያይ ተረጋግጧል፡፡ ተጫዋቹ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የሚጠናቀቅ በመሆኑ በነፃ ዝውውር ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በክለቡ…

በእግር ኳስ ህይወቱ ቀይ ካርድ ያለተመለከተው ኢኔሽታ …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ላማስያ አካዳሚ በመነሳት እልፍ አእላፍ ስኬቶችን የተጎናፀፉ አሉ። እንደእነ ሊዮኔል ሜሲ፣ ዣቪ ሄርናንዴዝ እና ሰርጂዮ ቡስኬት የመሳሰሉ ተጨዋቾች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። ስፔናዊው የባርሴሎና የቀድሞ የመሀል ሜዳ ተጫዋች አንድሬስ ኢኔሽታም ከዋነኞቹ አንዱ ነው። በተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ጭምር…

ኢትዮጵያ መድን ሀዋሳ ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ መሪነቱን ማጠናከር ችሏል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ አበራና አቡበከር ሳኒ ሲያስቆጥሩ ÷የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ ቸርነት አውሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡…