ስፓርት
በሊዝበን ግማሽ ማራቶን አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በፖርቹጋል ሊዝበን ከተማ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ አሸንፋለች፡፡
አትሌት ፅጌ ርቀቱን 1 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡
ኬንያዊቷ አትሌት ሩዝ ቼፕንጌቲች 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ በመግባ 2ኛ ደረጃን ስትይዘ ለስዊድን የምትሮጠው አትሌት አበባ አረጋዊ ደግሞ 3ኛ በመሆን አጠናቅቃለች፡፡
Read More...
ማንቼስተር ዩናይትድ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ አርሰናልን ያስተናግዳል።
ደካማ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኘውና በሁሉም ውድድር ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል ማድረግ የተሳነው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል።…
ማንቼስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ 9ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኖቲንግሃም ፎረስት ማንቼስተር ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
9 ሠዓት ከ30 ላይ በተደረገው ጨዋታ፤ የኖቲንግሃም ፎረስትን ብቸኛ ጎል ካሉም ሁድሰን ኦዶይ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የአሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን ኖቲንግሃም ፎረስት፤ ነጥቡን ወደ 51 ከፍ በማድረግ…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሥድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሥድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በወጣው መርሐ-ግብር መሠረት 9 ሠዓት ከ30፤ ኖቲንግሃም ፎረስት በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡
በውድድር ዓመቱ አስገራሚ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የአሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን ኖቲንግሃም ፎረስት፤…
ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያከናውናል።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ፤ በኦሌምቤ ስታዲየም ምሽት 3 ሠዓት ላይ ይደረጋል፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያ ሙሉ ቢጫ መለያ እንደምትጠቀም መገለጹን የእግር ኳስ…
ኢትዮጵያ መድን ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ መሃመድ አበራ በ70ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን ነጥቡን ወደ 38 ከፍ በማድረግ የሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል፡፡…
ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለወላይታ ድቻ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አብነት ደምሴ አስቆጥሯል።
ፈረሰኞቹ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ30 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ…