የገና በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር ገብተዋል- ፖሊስ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የገና በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የፀጥታ አካላት የጋራ እቅድ በማውጣት ለቅድመ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባር ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎችና በትራንስፖርት መጠበቂያ ቦታዎች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ፖሊስ ተሰማርቷልም ነው የተባለው፡፡
የዘንድሮው የገና በዓል በሰላም እንዲከበር የከተማዋ ነዋሪዎች የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ነፃ ስልክ ወይም
• አዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ 011-1-1-01-11
•አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-2-73-37-43
• አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-1-57-34-26
• ኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-3-71-77-53
• ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-1-57-50-59
• ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-5-15-37-60
• የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-6-18-13-39
• ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-5-52-80-44
• ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-6-67-47-18
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-4-40-07-92
• አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-4-39-14-38
• ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-6-39-10-24 መስመሮችን መጠቀም እንደሚቻል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።