Fana: At a Speed of Life!

የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ የመጀመሪያው 14 ኪሎ ሜትር ከቢሻን ጉራቻ በመነሳት ወደ ሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሄድ ነው።
የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ መዳረሻው ስለሚያደረግ በዋናነትም ለሲዳማ እና ደቡብ ክልሎች የአየር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ምቹ መሰረተ ልማትን ዕውን በማድርግ ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተነግሯል።
ለሐዋሳ ሀይቅ እና ለአካባቢው ተደራሽ በመሆኑ የቱሪዝም ፍሰትን እንዲጨምር በማድረግ ረገድም ሚናው ላቅ ያለ መሆኑና በሐይቁ ውስጥ የሚገኘውን ከፍተኛ የዓሳ ምርት በአጭር ጊዜ ወደ ገበያ ለማውጣትም ያስችላል ነው የተባለው።
ከዚያም ባለፈ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚመረቱ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የተለያዩ አልባሳትን መንገዱን በመጠቀም ወደ ሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ለማድረስ ይረዳል ነው የተባለው።
መንገዱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የወሰደው 592 ሚሊየን 84 ሺህ ብር ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን፥ የመንገዱን ግንባታ አለም አቀፉ የስራ ተቋራጭ ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ አከናውኖታል።
በማማከርና በቁጥጥር ስራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን መሳተፉን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.