ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የዲላ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ቡድን ጉዳት ለደረሰበት ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደርጓል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ተወካይ ዶክተር ዳዊት ሀዬሶ ከዩኒቨርሲቲው ለተደረገው ድጋፍ ሽኝት አድርገዋል።
በአሸባሪው የህወሓት ቡድን በርካታ ተቋማቶች መውደማቸውን የገለፁት ዶክተር ዳዊት ፥ ከእነዚህ ተቋማት መካከል ደግሞ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ አንዱ በመሆኑ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ27 በላይ የሚደርሱ የትምህርት፣ የክሊኒክ እና ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ግብዓቶች በገንዘብ ሲተመን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ለውጥ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር እና የድጋፍ ቡድኑ አስተባባሪ አቶ ይመኑ ዳካ በበኩላቸው፥ ድጋፉ የአብሮነት መገለጫ እንደሆነ ገልጸው፥ በቀጣይም በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የፈረሱ ተቋማትን መልሶ የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸዉን ከዩኒቨርሲቲዉ ያገኘነዉ በመረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!


0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like
Comment
Share