Fana: At a Speed of Life!

ሦስተኛው የሩሲያ-ዩክሬን የሰላም ውይይት ተጨባጭ ውጤት ማምጣት አልቻለም ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስተኛው የሩሲያ-ዩክሬን የሰላም ድርድር ተጨባጭ ውጤት ሳያመጣ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

የሩሲያ ልዑካን ቡድን መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ ከውይይቱ በኋላ እንደተናገሩት÷ በፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ውይይት ምንም የረባ ለውጥ ሳያመጣ ተጠናቋል፡፡

ከድርድሩ የተጠበቀውን ውጤት ማምጣት ባይቻልም በቀጣይ መድረክ የተሻለ ነገር እንደሚጠብቁም ገልጸዋል፡፡

የሩሲያ ተደራዳሪዎች ልዩ ስምምነቶችን ጨምሮ በርከት ያሉ የመደራደሪያ ሰነዶች ይዘው የመጡ ቢሆንም በዩክሬን በኩል ሰነዱን እንደገና እናየዋለን በማለት ስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸው ታውቋል፡፡

በዚህ የሰላም የድርድር መድረክ በፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጉዳይ ላይ አንዳችም እርባና ያለው ውጤት ባይመጣም የሰብአዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ግን አወንታዊ ውይይቶች ተደርገዋል ተብሏል፡፡

የሁለቱም ወገን ተደራዳሪዎች በጦርነቱ የሚፈናቀሉ ወገኖችን በተመለከተ በትኩረት መክረዋል፡፡

የዩክሬን ተደራዳሪዎች ሰብአዊ መተላለፊያ ኮሪደሮችን በአስቸኳይ ሥራ እንደሚያስጀምሩ ለሩሲያ አረጋግጠዋል መባሉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.