Fana: At a Speed of Life!

ሐምሌ 19 የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል የንግሥ በዓል በሰላም ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ ሐምሌ 19 የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል እና በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተከብሯል፡፡

የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምርያ ሃላፊ ኮማንደር ናስር መሀመድ በቁልቢ ገብርኤል የተከበረውን የንግስ በዓል አስመልክተው እንደገለጹት ÷ በዓሉ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ከአገር ውስጥና ከውጪ የመጡ ምዕመናን እና ሌሎች እንግዶች ታድመውበታል።

በዓሉ በደመቀ ሃይማኖታዊ ሥነ ሰርዓትና በሰላማዊ ሁኔታ መከበሩንም ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡

በቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ላይ የተገኙት ምዕመናን በዓሉ በሰላም መጠናቁን ተከትሎ ፈጣሪያቸውን በማመስገን ወደ የመጡበት አካባቢ በመመለስ ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በተመሳሳይ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሀዋሳ ቅዱስ ገብርዓል ገዳም በርካታ ሕዝብ በተገኘበት በድምቀት የተከበረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ÷ ከበዓሉ በኋላ በከተማዋ ቆይታ ለሚያደርጉ እንግዶች ምቾታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

ከሻሸመኔና ከሌሎች ከተሞች በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እና ወደቤታቸው ለሚመለሱ የእምነቱ ተከታዮች በየመናኸሪያው በሚገኙ አካላት ከትራንስፖርት አቅርቦት ጋር በተያያዘ የማመቻቸትና የማስተናበር ስራን በየመንገዱ ከሚገኙ የመንገድ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጀምሮ ከፍተኛ ስራ በመሰራት ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በበዓሉ ላይ የተሰየመው ጊዜያዊ ምድብ ችሎት ሁለት ግለሰቦች የሞባይል ስርቆት ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በመቅረባቸው ጉዳያቸው ወዲያው ታይቶ የሁለት ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል ብለዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግና

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.